የኬንያ ሙሰኞች ከመንግስትና ህዝብ የመዘበሩትን ገንዘብ በሀገር ውስጥ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ተጠየቁ
የኬንያ ባለስልጣናት በየዓመቱ ከሁለት ቢሊዮን በላይ ዩሮ ወደ ውጪ ሀገር እንደሚያሸሹ የዓለም ባንክ አስታውቋል
የሀገሪቱ ኦዲተር ቢሮ የኬንያ ሙሰኞች የመዘበሩትን ገንዘብ ቢያንስ ከሀገር ውጪ እንዳያሸሹ አሳስቧል
የኬንያ ሙሰኞች ከመንግስት እና ህዝብ የመዘበሩትን ገንዘብ በሀገር ውስጥ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ተጠየቁ።
ጎረቤት ሀገር ኬንያ በስልጣን ላይ ያሉ የሀገሪቱ ሙሰኞች ከህዝብ እና መንግስት የመዘበሩትን ገንዘብ ቢያንስ በሀገር ውስጥ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ተማጽናለች።
የሀገሪቱ ኦዲተር ቢሮ እንዳለው ከሆነ ምንጫቸው ያልታወቀ ገንዘብ ወደ ልማት እንዲቀየሩ ቢፈቀድ ኬንያ በአጭር ጊዜ ውስጥ እድገት ልታስመዘግብ ትችላለች ሲል አስታወቋል።
የቢሮው ዋና ዳይሬክተር ናንሲ ጋቱንጉ እንዳሉት የኬንያ ባለስልጣናት ከህዝብ እና መንግስት የመዘበሩትን ገንዘብ ከማሸሽ ይልቅ እዚሁ ሀገራቸው ውስጥ ኢንቨስት ቢያደርጉት የተሻለ ነው ብለዋል።
ባለስልጣናቱ ከኬንያዊያን ከሰረቁ በኬንያ ኢንቨስት ሊያደርጉ ይገባል ይህ ከሆነ ነገ ገንዘቡን ከየት አመጣችሁት ብለን ወደ መጠየቅ እንሄዳለን ሲሉም አክለዋል።
የዋና ኦዲተሯን አስተያየት ተከትሎም ጉዳዩ በኬንያ ዋነኛ መነጋገሪያ አጀንዳ የሆነ ሲሆን ሁለት አይነት አስተያየቶች ከህዝቡ በመንጸባረቅ ላይም ናቸው።
የመጀመሪያው ሀሳብ በዋና ኦዲተሯ ሀሳብ ተስማምተው ሀሳባቸው ሲያጋሩ ቀሪዎቹ ደግሞ እርስዎንም የሾምነው ምዝበራን እንዲቆጣጠሩልን ነበር ሲሉ ትችቶችን ሰንዝረዋል።
እንደ ዓለም ባንክ መረጃ ከሆነ የኬንያ በለስልጣናት በየዓመቱ 2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር በመመዝበር ወደ ሌሎች ሀገራት ያሸሻሉ።