ኬንያ በሀገሪቱ በሚገኙ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ላይ ዘመቻ ጀመረች
የኬንያ ብሄራዊ ፖሊስ የኦሮሞ ነጻት ሰራዊት ኢላማ ያደረገ ዘመቻ በማርሳቢትና ኢሲዮሎ መክፈቱን አስታውቋል
የኬንያ ፖሊስ የኦሮሞ ነጻት ሰራዊትን ለድንበር ተሻጋሪ የወንጀል ድርጊቶች ተጠያቂ አድርጓ
የኬንያ ብሄራዊ ፖሊስ በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል አካባቢ በሚገኙ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን ኢላማ ያደረገ ዘመቻ በይፋ መጀመሩን አስታውቋል።
የኬንያ ብሄራዊ ፖሊስ በኤክስ ይፋዊ ገጹ ባጋራው መረጃ በማርሳቢትና ኢሲዮሎ አካባቢ በሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነጻት ሰራዊት ላይ ዘመቻ መክፈቱን ገልጿል።
ልዩ የተባለው የደህንነት ዘመቻው በተከታታይ የድንር ዘለል ወንጀሎች ተጠያቂ የሆነው የኦሮሞ ነጻት ሰራዊት ላይ ያነጣጠረ መሆኑንም ፖሊስ በመግለጫው አስታውቋል።
የኬንያ ብሄራዊ ፖሊስ ትናንት ሰኞ ጥር 26 በሰጠው መግለጫ "ወንጀለኞችን የማስወገድ ኦፕሬሽን" በማርሳቢትና ኢሲዮሎ ውስጥ በተለይም በሶሎሎ፣ ሞያሌ፣ ሰሜን ሆር እና መርቲ አካባቢዎች ተደብቀው የሚገኙ የኦሮሞ ነጻት ሰራዊት ወንጀለኞችን ለማጥፋት ያለመ መሆኑን አስታውቋል።
የኬንያ ፖሊስ የኦሮሞ ነጻት ሰራዊትን በህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ እና አደንዛዥ እጽ ዝውውር፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር፣ የኮንትሮባንድ እቃዎች ንግድ፣ ህገ-ወጥ ማዕድን ማውጣት፣ የጎሳ ግጭቶችን በማነሳሳት እና ሰዎችን አግቶ ገንዘብ በመቀበል ወንጀሎች ይከሳል።
የኦሮሞ ነጻት ሰራዊትን በፈረንቹ 2005 በቱርቢ የተካሄደውን እልቂት ጨምሮ በተለያዩ ግጭቶች ውስጥ ተሳትፏል በሚልም ይከሰሳል።
የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት በኬንያ ብሄራዊ ፖሊስ ለቀረቡበት ውንጀላ እስካሁን በይፋዊ ገጹ የሰጠው ምላሽ የለም።
የኢትዮያ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ባለንት ጥር ወር መጀመሪያ ላይ ወደ ናይሮቢ አቅንተው ከኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር መነጋራቸው ይታወሳል።
የኬንያው የብሔራዊ መረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል ኑረዲን ሐጂ በተገኙበት በተደረገው ውይይት ላይም ኢትዮጵያ እና ኬኒያ ሽብርተኝነትን ጨምሮ የተደራጁ ወንጀሎችን በጋራ መካላከል በሚችሉበት አግባብ ላይ ምክክርመደረጉም በወቅቱ ተነግሯል።