አልፍሬድ ሙቱዋ የኬንያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ተደርገዋል
ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ አዲስ ካቢኔያቸውን አዋቀሩ።
ጎረቤት ሀገር ኬንያ ከሁለት ሳምንት በፊት ዊሊያም ሩቶን ፕሬዝዳንት አድርጋ መሾሟ ይታወሳል።
አዲሱ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ቃለ መሀላ በፈጸሙ በማግስቱ ካቢኔያቸውን ያዋቅራሉ በሚል ተጠብቀው የነበረ ቢሆንም ለሁለት ሳምንታት ዘግይተዋል።
ፕሬዝዳንቱ 22 አባላት ያለው ካቢኔያቸው ይፋ ያደረጉ ሲሆን 33 በሙቶዎቹ ሴት የካቢኔ አባላት እንደሆኑ ተገልጿል።
በፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ወቅት ዊሊያም ሩቶን ሲያግዙ የንበሩት ሪጋቲ ጋቻንጉዋ የኬንያ ምክትል ፕሬዝዳንት ሲሆኑ የቀድሞው የኬንያ ቃል አቀባይ የነበሩት አልፍሬድ ሙቱዋ ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ተደርገዋል።
እንዲሁም ርብቃ ሚያኖ ደግሞ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ሀላፊ ሲደረጉ ሙሳሊያ ሙዳቫዲ ደግሞ የኬንያ ጠቅላይ ሚንስትር ሆነው መሾማቸውን ሲጂቲኤን አፍሪካ ዘግቧል።
ፕሬዝዳንቱ ከዚህ በተጨማሪ የትምህርት ፣ ግብርና፣ ንግድ ፣ ጤና፣ አካባቢ ጥበቃ፣ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች፣ መከላከያ ሚንስትሮችንም ሾመዋል ተብሏል።
አዲሱ የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በኮሮና ቫይረስ፣ ድርቅ ፣ የነዳጅ እና ምግብ ዋጋ መናር እና አለመረጋጋቶች የተጎዳውን ኢኮኖሚ እንዲያገግም ማድረግ ዋነኛ ስራቸው እንደሚሆን ከዚህ በፊት መናገራቸው ይታወሳል።
ፕሬዝዳንት ዊሊያም ከቀናት በፊት በተጥናቀቀው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ የበለጸጉ ሀገራት ለታዳጊ ሀገራት የእዳ ስረዛ እንዲያደርጉ መጠየቃቸው ይታወሳል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም ሀገራቸው የገጠማትን የነዳጅ እጥረት ለማስታገስ የሩሲያን ነዳጅ እንደሚገዙም ተናግረዋል።