ኬንያ በጤና ስጋት ምክንያት የዴንማርክ መርከብ ኳራንታይን ተደርጋ እንድትቆይ አዘዘች
ኬንያ መርከቧን እንድትገለል የወሰነችው የዜጎች ጤናን አደጋ ላይ የሚጥል የሬዲዮአክቲቭ ቁሶች ይዛለች በሚል ነው
የኬንያ የኑክሌር እና ቁጥጥር ባለስልጣን ጥያቄ የተነሳበትን የራዲዮአክቲቭ ንጥረ ነገር እና መጠን ይመረምራልም ተብሏል
ኬንያ ዜጎቿን ሊመርዝ ይችላል በሚል ፍራቻ ሬዲዮአክቲቭ ቁሶችን የያዘች የዴንማርክ መርከብ ኳራንታይን እንድትደረግ ማዘዟን አስታወቀች።
የካቢኔ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሙታሂ ካግዌ እንደተናገሩት ሴጎ ፒሬየስ፡ መርከቧ የያዘቻቸው የVoy 1475 B/L214735979 የሬዲዮአክቲቭ ንጥረ ነገሮች ልቀት የኬንያውያንን ጤና እና ህይወት አደጋ ላይ የሚጥል ነው ማለታቸውንም ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ዘግቧል፡፡
ካግዌ በኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ በሰጠጡት መግለጫ “መርከቧ ማንኛውንም ክፍል ለመፈተሽ እና እንዲሁም በመርከቧ ላይ ያለ ማንኛውም ሰው ላይ የህክምና ምርመራ ለማድረግ ሲባል ተገላ መቆየት አለባት” ሲሉ ተናግሯል ።
በመርከቧ ላይ ያለ ማንኛውም ሰው በኬንያ የህብረተሰብ ጤና ህግ መሰረት ለጥያቄዎች መልስ መስጠት እንደሚጠበቅበት ጠቁሟል።
የኬንያ የኑክሌር እና ቁጥጥር ባለስልጣን (Kenya Nuclear and Regulatory Authority) ጥያቄ የተነሳበትን የራዲዮአክቲቭ ንጥረ ነገር እና መጠን ለማወቅ የእቃውን ይዘት ይመረምራልም ብሏል ሚኒስትሩ ካግዌ ።
የካቢኔ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሙታሂ ካግዌ ኬንያ ዓለም አቀፍ ሰነዶችን ካጸደቁ ሀገራት አንዷ በመሆኗ የራዲዮአክቲቭ እና የኒውክሌር ዕቃዎችን ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን እና የጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎችን የመከላከል፣የማገድ፣የመከልከል እና የመዋጋት ዓለም አቀፍ ግዴታ አለባትም ብሏል።