በኬንያ የምርጫ ውጤት ቅሬታ በመቅረቡ ጉዳዩን የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያየዋል
በኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለ5ኛ ጊዜ በዕጩነት የቀረቡት ራይላ ኦዲንጋ ትናት ይፋ የተደረገውን የምርጫ ውጤት እንደማይቀበሉ አስታውቀዋል።
የኬንያ ብሔራዊ የምርጫ ኮሚሽን ትናንት ዊሊም ሳሞይ ሩቶ ማሸነፋቸውን ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ቢሆንም ዛሬ ግን ኦዲንጋ አልቀበልም ብለዋል።
ራይላ ኬንያን በፕሬዝዳነትንት ለመምራት 5 ጊዜ በዕጩነት ቢቀርቡም ትናንትም አልተሳካላቸውም። የ 77 ዓመቱ ራይላ ኦዲንጋ ከምርጫው ውጤት መገለጽ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ጋዜጣዊ መግለጫም ሰጥተዋል።
ራይላ ኦዲንጋ የፕሬዝዳንታዊ ምርጫው ውጤት ተቀባይት እንደሌለውና እርሳቸውም እንደማይቀበሉት ተናግረዋል። በፓርቲያቸው የሚዲያ ክፍል በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ውጤቱ ተቀባይነት የለውም።
የኦዲንጋ ደጋፊዎች “ካለ ኦዲንጋ ሰላም የለም” በማለት ምሽቱን ጀምሮ ተቃውሞ ቢያነሱም ኮሚሽኑ ግን በውጤቱ ሩቶ አሸንፈዋል ብለዋል።
የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤትን እንደማይቀበሉም አራት የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አባላት ተናግረዋል። ሁለት የምርጫ ኮሚሽን አባላት ደግሞ ህይወታቸው አልፏል።
ለአምስተኛ ጊዜ እየተወዳደሩ ያሉት ኦዲንጋ ዛሬ እንደገለጹት ከሆነ የሩቶን ውጤት ተቀባይነት የለውም።
የ 77 ዓመቱ ፕሬዝዳንታዊ እጩ በምርጫው አሸንፈው ስልጣን ከያዙ በኬንያ ታሪክ የመጀመሪያዋን ሴት ምክትል ፕሬዝዳንት እንደሚሾሙ ቃል ገብተው ነበር።
ራይላ ኦዲንጋ የቀድሞዋን የሀገሪቱን ፍትህ ሚኒስትር ማርታ ካሩዋን መርጠው የምረጡኝ ቅስቀሳቸውን አድርገው የነበረ ቢሆንም ሽንፈት ገጥሟቸዋል፡።
ትናንትና ምሽት ይፋ በተደረገው ውጤት መመረጣቸው የተረጋገጠው ሩቶ ህዝቡንና ምርጫ ኮሚሽኑን አመስግነው ነበር።