ፕሬዝዳንት ኬንያ ሀገሪቱ ያለባትን 80 ቢሊዮን ዶላር እዳ ለመክፈል የግብር ጭማሪ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል
ኬንያ በዳቦ ላይ ልትጥለው ያሰበችውን ግብር ሰረዘች፡፡
በጎረቤት ሀገር ኬንያ መዲና ናይሮቢ መንግስት ያዘጋጀውን የቀረጥ ረቂ ህግ እንዲሰርዝ የሚጠይቁ ሰላማዊ ሰልፎች ሲካሄዱ ቆይተዋል፡፡
ከሰሞኑ እንደ አዲ የተጀመረው ይህ የሕዝብ ተቃውሞ የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ መንግስት ያዘጋጀውን ረቂቅ የቀረጥ ወይም ግብር ህግ በተወሰኑት ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
በዛሬው ዕለትም በዳቦ ላይ ሊጣል የነበረው የ16 በመቶ ግብር ተሰርዟል የተባለ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ የሕዝቡን ኑሮ ውድነት ያባብሰዋል በሚል እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ይሁንና ኬንያዊያን አሁንም የፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ መንግስት በምግብ ነክ ምርቶች ላይ ያዘጋጀውን ረቂቅ ህግ እንዲሰርዝ በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡
ኬንያ በአጼ ሀይለስላሴ ስም የሰየመችውን ፈጣን መንገድ አስመረቀች
ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ወደ ስልጣን እንደመጡ ኬንያዊያን በቂ ግብር እየከፈሉ እንዳልሆነ መናገራቸው ይታወሳል፡፡
እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለጻ ኬንያ 80 ቢሊዮን ዶላር የውጭ እዳ ያለባት ሲሆን እዳዋን ለመክፈል ተጨማሪ ገቢ ማስገኘት የሚያስችሉ የግብር ክፍያ ማሻሻያዎችን በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
ከተዘጋጁ የግብር ረቂቅ ህጉ መሰረት ጭማሪ ከሚደረግባቸው ምርቶች መካከል የፕላስቲክ እና ኤሌክትሮኒክስ ምርቶች፣ ማሸጊያ ምርቶች ዋነኞቹ ሲሆኑ ኬንያዊያን ይህን በመቃወም ላይ ናቸው፡፡