እየሱስን ለማግኘት ተራቡ በሚል ለብዙዎች ሞት ምክንያት የነበረው ተጠርጣሪ ህይወቱ አለፈ
ግለሰቡ በፖሊስ መታሰሩን በመቃወም በረሃብ አድማ ላይ ነበር ተብሏል
በኬንያ እየሱስን ለማግኘት በሚል በረሃብ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 336 አሻቅቧል
እየሱስን ለማግኘት ተራቡ በሚል ለብዙዎች ሞት ምክንያት የነበረው ተጠርጣሪ ህይወቱ አለፈ፡፡
በኬንያ በሰባኪ ወይም ፓስተር ፖል ንቴንጌ አስተባባሪነት እየሱስ ክርስቶስን ለማግኘት ተራቡ በሚል በተላለፈ ትዕዛዝ ምክንያት በርካቶች ህይወታቸውን ማጣታቸው ይታወሳል፡፡
በዚህ ሰባኪ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር በየጊዜው የጨመረ ሲሆን ፖሊስም ሰባኪ ፖልን ጨምሮ 30 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር አውሏል፡፡
እስካሁን ህይወታቸውን ያጡ ምዕመናን ቁጥር 336 ደርሷል የተባለ ሲሆን በፖሊስ ከታሰሩት መካከል ጆሴፍ ጁማ የተሰኘ ተጠርጣሪ እስሩን በመቃወም በረሃብ አድማ ለይ እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
"ጂቡቲና ኬንያ ግብይት ለመፈጸም ዶላር አያስፈልጋቸውም" - ፕሬዝዳንት ሩቶ
ይህ ግለሰብም ለህክምና በተወሰደበት ሞምባሳ ሆስፒታል ዛሬ ህይወቱ እንዳለፈ የሀገሪቱ ከፍተኛ አቃቢ ህግ ለፍርድ ቤት አስረድቷል፡፡
ፖሊስ ተጨማሪ ዜጎች በሰባኪ ፖል ትዕዛዝ እየሱስን ለማግኘት ሲሉ ራሳቸውን አስርበው የገደሉ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ጥርጣሬ እንዳለው የገለጸ ሲሆን 600 ሰዎች አሁንም የት እንዳሉ እንዳልታወቀም ተገልጿል፡፡
በዚህ ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥ ተጨማሪ ሁለት ሰዎች አሁንም በረሃብ አድማ ለይ ናቸው የተባለ ሲሆን ለህክምና ወደ ሌላ ሆስፒታል መወሰዳቸው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
የኬንያ አቃቢ ህግ እስካሁን በተጠርጣሪዎቹ ላይ ክስ ያልመሰረተ ሲሆን ታሳሪዎቹ ለተጨማሪ ሁለት ወራት በማረሚያ ቤት እንዲቆዩ ለማስፈቀድ ፍርድ ቤቱን ሊጠይቅ ይችላልም ተብሏል፡፡