"ህጻናትን በተዓምር አስወልዳለሁ" በሚል የሚታወቁት ፓስተር ጊልበርት ከእስር ተለቀቁ
የድሀ ኬንያዊያን ህጻናትን በመስረቅ ተዓምር እሰራለሁ የሚሉት እኝህ ግለሰብ በኬንያ ታስረው ነበር
ፓስተሩ በተለይም መጸነስ ያልቻሉ እንስቶች ያለምንም ግንኙነት በአራት ወራት ውስጥ ልጅ እንዲወልዱ አደርጋለሁ በሚልም ዝነኛ ሰው ሆነዋል
"ህጻናትን በተዓምር አስወልዳለሁ" በሚል የሚታወቁት ፓስተር ጊልበርት ከእስር ተለቀቁ።
ታዋቂው ኬንያዊ ፓስተር ጊልበርት ዴያ በአፍሪካ እና በአውሮፓ ህጻናትን በተዓምር አስወልዳለሁ በሚል ይታወቃሉ።
በተለይም ልጅ መውለድ ያልቻሉ ጥንዶች ወደ ቤተክርስቲያናቸው ቢመጡ ጸሎት በማድረግ ልጅ በተዓምር አስታቅፋለሁ በሚልም ይታወቃሉ።
ፓስተሩ በተለይም መጸነስ ያልቻሉ እንስቶች ያለምንም ወሲባዊ ግንኙነት በአራት ወራት ውስጥ ልጅ እንዲወልዱ አደርጋለሁ በሚልም ዝነኛ ሰው ሆነዋል።
- “ኢየሱስን ለማየት ተራቡ” በሚል 58 ሰዎች ህይወታቸው እንዲያልፍ ያደረገው ፓስተር ተያዘ
- የደቡብ አፍሪካው ፓስተር አስከሬን "ትንሳኤ" ሲጠበቅ 579 ቀናትን ሳይቀበር መቆየቱ ተነገረ
በ1990ዎቹ አምስት ህጻናትን ከድሀ ኬንያዊያን በመስረቅ ቤተ ክርስቲያናቸው ለሚሰራው "ሚራክል ቤቢስ" ወይም "የተዓምር ልጆች? ፕሮግራም በማዋል የህጻናት ስርቆት ፈጽመዋል በሚል ክስ ቀርቦባቸዋል ሲል ቪኦኤ ዘግቧል።
ፓስተር ጊልበርት ከተመሰረተባቸው ክስ ለማምለጥ ሲሉም ወደ ለንደን በኋላም ወደ ስኮትላንድ የኮበለሉ ቢሆንም በኢንተርፖል አማካኝነት ለኬንያ ተላልፈው ተሰጥተዋል።
ላለፉት ስድስት ዓመታት በናይሮቢ እስር ቤት ያሳለፉት የ86 ዓመቱ አዛውንት የተመሰረተባቸውን ክስ ስለ መፈጸማቸው ማስረጃ እንዳልተገኘ ተገልጿል።
ፓስተር ጊልበርት ወደ ሀይማኖት ሰባኪነት ከመምጣታቸው በፊት የድንጋይ ጠረባ አልያም ማስዋብ ስራ ባለሙያ ነበሩ ተብሏል።
ከእስር የተለቀቁት ፓስተር ጊልበርት ክስ በመሰረቱባቸው እና በእስር ቤት ሆኜ ማየት ለፈለጉ ሁሉ ይቅርታ አድርጌያለሁ ሲሉ ተናግረዋል።
ኬንያ ከአራት ሺህ በላይ ቤተክርስቲያን ያላት ሲሆን ብዙዎቹ የስነ መለኮት ትምህርት ያልተማሩ እና የራሳቸውን ስታይል የሚከተሉ ናቸው ተብሏል።