የደቡብ አፍሪካው ፓስተር አስከሬን "ትንሳኤ" ሲጠበቅ 579 ቀናትን ሳይቀበር መቆየቱ ተነገረ
ፓስተሩ ዳግም ይነሳሉ በሚል አስከሬናቸው እስኪበሰብስ ድረስ ሳይቀበር ቆይቷል
የፓስተሩ ቤተ-ክርስቲያን "በአፋጣኝ ፈውስ" የሚያምን እንደሆነ ተነግሯል
በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው ቀብር አስፈጻሚ ባለፈው ሳምንት የ53 ዓመቱን ፓስተር አስከሬን ለመቅበር የፍርድ ቤት ትእዛዝ ተቀብሏል።
የፓስተሩ አስከሬን ለሁለት ዓመታት ያህል በማቆያ ክፍል ውስጥ ቆይቷል ነው የተባለው።
ፓስተር ሲቫ ሙድሊ በፈረንጆቹ ነሀሴ 14፣ 2021 ህይወታቸው ቢያልፍም፤ ቤተሰባቸው ከሞት እንደሚነሱ ስላመኑ አስከሬኑ በጆሃንስበርግ በሚገኝ ቀብር ቤት ቆይቷል።
የጋውቴንግ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስከሬኑ ከአንድ ዓመት በላይ ማቆያ ቤት መቆየቱ የጤና ስጋት በማሳደሩ ቀብሩ እንዲፈጸም ትእዛዝ ተሰጥቷል።
ቀብር አስፈጻሚው 28 ጊዜ የፓስተሩን አስከሬን ቤተሰቡ እንዲረከበኝ ብጠይቅም ሰሚ አጥቻለሁ ብሏል።
ፓስተሩ ህይወታቸው ካለፈ ከ579 ቀናት በኋላ ቤተሰቦቻቸው አስከሬኑን አለመጠየቃቸው ተናግሯል።
የሟች ሚስት ባላቸው ከሞት ሊነሳ እንደሚችል ራዕይ እንዳዩ ተናግረው ነበር ተብሏል።
በፓስተሩ የፍርድ ቤት ትእዛዝ የቀብር ስነ-ስርዓት ላይ ባለቤታቸውና ልጃቸው አለመገኘታቸውን ሲቲዝን ዲጂታል ዘግቧል።
የፓስተሩ አስተምሮና ቤተ-ክርስቲያን "በአፋጣኝ ፈውስ" የሚያምን እንደሆነ ተነግሯል።