ቁልፍ የሚባሉት የድህነት መለኪያውች ምንድናቸው?
ዘርፈብዙ እና ውስብስብ የሆነው ድህነት በዓለም ዙሪያ ባሉ በሚሊዮን በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ተፍእኖ እያሳደረ ይገኛል
ብዙ ጊዜ ድህነት የቁስ ማጣት ተደርጎ ቢታይም ቢሆንም የድህነት ተፈጥሮ ግን ገንዘብ ከማጣት የዘለለ ነው።
ቁልፍ የሚባሉት የድህነት መለኪያውች ምንድናቸው?
ዘርፈብዙ እና ውስብስብ የሆነው ድህነት በዓለም ዙሪያ ባሉ በሚሊዮን በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ተፍእኖ እያሳደረ ይገኛል።
ብዙ ጊዜ ድህነት የቁስ ማጣት ተደርጎ ቢታይም ቢሆንም የድህነት ተፈጥሮ ግን ገንዘብ ከማጣት የዘለለ ነው።
ይህ ጽሁፍ ቁልፍ የሚባሉ የድህነት መለኪያዎችን ያብራራል።
እነዚህ የድህነት መለኪያዎች ፖሊሲ አውጭዎች፣ ተመራማሪዎች እና ድርጅቶች የድህነትን ዘርፈ ብዙ ገጽ እንዲረዱ ያስችሏቸዋል።
1. የገቢ መጠን
አንደኛው የድህነት መለኪያ የገቢ መጠን ነው። የገቢ መጠን ከተቀመጠው የድህነት ልኬት ጋር ሲነጻጸር ዝቅ ካለ ድህነት ወላል ላይ ናቸው ማለት ይቻላል
2. ፖቨርቲ ሄድ ካውንት ሬሾ
ምን ያህል ህዝብ ከድህነት ወለል በታች ነው የሚለው የሚሰላበት ዘዴ ነው።
3.ፖቨርቲ ጋፕ
ፖርቲ ጋፕ የድህነቱን መጠን ማጥኛ ዘዴ ነው። ከአጠቃላይ ህዝቡ በአማካኝ ምን ያህል ሰው ከድህነት ወለል በታች ወርዷል የሚለውን ያጠናል።
4. መልቲ ዳይሜንሽናል ፖቨርቲ እንዴክስ(ኤምፒአይ)
ድህነት የገንዘብ ጉዳይ ብቻ አይለም ብሎ እውቀና በመስጠት እንደ ጤና፣ ትምህርት እና የኑሮ ደረጃን ጨምሮ በርካታ ሁኔታዎችን ይገመግማል። ይህ ዘዴ ድህነትን በጥልቀት ለመረዳት የሚያስችል ነው።
5. የስራ አጥነት ምጥነት
ስራ አጥነት ለድህነት መኖር ወሳኝ ሚና ይጫወታል። የስራ አጥነት ምጥነት የስራ አጥ ሰዎችን የሚያመለክት ስለሆነ ወሳኝ የድህነት ጠቋሚ ሆኖ ያገለግላል።
6. የመሰረታዊ ፍላጎቶች አቅርቦት
የንጽህና፣ የጤና፣ የትምህርት እና የመጠጥ ውሃ አገልግሎቶች የአንድን ሰው የኑሮ ደረጃ ይወስናሉ። ይህ መለከያ ያለውን የህዝብ ቁጥር ከእነዚህ አገልግሎቶች ጋር ያለውን ምጥነት ያሰላል።
7. የትምህርት ደረጃ (ሊትሬሲ ሬት)
ትምህርት ሁል ጊዜ ከድህነት ማምለጫ መንገድ ተደርጎ ይቆጠራል። የትምህርት ደረጃ ምን ያህል ማንበብ እና መጻፍ የሚችለውን ለማወቅ የሚረዳ ነው።
ምንምእንኳን የገቢ መጠን ዋነኛ የድህነት መለኪያ ቢሆንም ድህንትን ለመረዳት ጠቅላላ የሆኑ ሁኔታዎችን ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልጋል።