የአሜሪካ ጦር ሄሊኮፕተር በተጋጨበት ወቀት ወሳኝ የደህንነት መጠበቂያ ስርአቱ ጠፍቶ ነበር ተባለ
በግጭቱ በሄሊኮፕተሩ እና በመንገደኞች አውሮፕላን ላይ የነበሩ 67 ሰዎችን ህይወታቸው አጥተዋል

አዲኤስ-ቢ የአውሮፕላን እንቅስቀሴ ለመከታተል የሚያስችል ዘመናዊ የቅኝት ቴክኖሎጂ ነው
ባለፈው ሳምንት ዋሽንግተን በሚገኘው የሪገን አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ ከመንገደኞች አውሮፕላን ጋር የተጋጨው የአሜሪካ ጦር ሄሊኮፕተር ወሳኝ የደህንነት መቆጣጠሪያ ስርአቱ ጠፍቶ እንደነበር ሮይተርስ ዘግቧል።
በግጭቱ በሄሊኮፕተሩ እና በመንገደኞች አውሮፕላን ላይ የነበሩ 67 ሰዎችን ህይወታቸው አጥተዋል።
የአሜሪካ ሴኔት ኮሜርስ ኮሚቴ ሊቀመንበር ቴድ ክሩዝ ግጭቱ ሲፈጠር ለወታደራዊ ኤየርክራፍት የሚፈቀደው የሄሊኮፕተሯ 'አውቶማቲክ ዲፔንደንት ሰርቪላንስ-ብሮድካስት' (ኤዲኤስ-ቢ) ሲስተም ጠፍቶ ነበር ብለዋል።
"ይህ የልምምድ ተልኮ ስለሆነ ኤዲኤስ-ቢን ለማጥፋት አስገዳጅ ምክንያት አልነበረም" ሲሉ ክሩዝ ከናሽናል ትራንስፖርቴሽን ሴፍቲ ቦርድና(ኤንቲኤስቢ) ከፌደራል አቪየሽን አስተዳደር(ኤፍኤኤ) ጋር ወይይት ካደረጉ በኋላ ተናግረዋ።
በአሜሪካ ከ20 አመታት በኋላ ባለፈው ሳምንት ባጋጠመው ከባድ የአየር አደጋ የተጋጩት ሄሊኮፕተርና አውሮፕላን ፖቶማክ ወንዝ ውስጥ ገብተዋል።
ኤንቲኤስቢ ሄሊኮተሩ 100 ጫማ ከፍ በማለት ከተፈቀደው ርቀት በላይ ሲበር እንደነበረ ቀደም ሲል ገልጿል።
አዲኤስ-ቢ የአውሮፕላን እንቅስቀሴ ለመከታተል የሚያስችል ዘመናዊ የቅኝት ቴክኖሎጂ ነው። ሄሊኮፕተሮች በራዳር የሚታዩ ቢሆንም ኤዲኤስ-ቢ ግን የበለጠ ትክክል እንዲሚሆን ክሩዝ አስታውሰዋል።
ባለፈው ሳምንት በኮሚቴው የዲሞክራት አባል የሆኑት ሴናተር ማሪያ ካንትዌል ኤፍኤኤ ከ2018 ጀምሮ የሚደረጉ በረራዎች ለምን ኤዲኤስ-ቢ እንዲያጠፉ እንደፈቀደ ጠይቀዋል።
ኤፍኤኤ ከፍተኛ የአየር በረራ ፍስት ያባቸውን አውሮፕላን ማረፊያዎች መቃኘት እንደሚጀምር በትናንትናው እለት ገልጿል። ኤፍኤኤ ከግጭቱ በኋላ ቢያንስ እስከ የካቲት መጨረሻ አካባቢ ድረስ በሪገን አውሮፕላን ማሪፊያ አቅራቢያ በሚደረጉ የሄሊኮፕተር በረራዎች ላይ እገዳ የጣለ ሲሆን ዝቅተኛ ጥቅም ይሰጡ የነበሩት ሁለት ማኮብኮቢያዎችም ተዘግተዋል።
የፖሊስ፣ የጤናና ፕሬዝደንታዊ የትራስፖርት ሄሊኮተሮች የአየር ክልሉን በሚጠቀሙበት ወቅት የሲቪል አውሮፕላን በተመሳሳይ ቦታ እንዲበሩ እንደማይፈቀድላቸው ኤፍኤኤ ያወጣው ማስታወሻ ያሳያል።
የኤንቲኤስቢ ዳይሬክተር ጀኒፈር ሆመንዲ ከኮክፒት በተገቢው ሪከርድ መሰረት አብራሪው ናይት ቪዥን ጉግለረስ አድርጎ ነበር። ሄሊኮተሩ ከፖቶማህ ወንዝ መውጣቱን የተናገሩት ዳይሬክሯ ኤንቲኤስቢ የሄሊኮፕተር ኤዲኤስ-ቢ በግጭት ወቅት መጥፋቱን ለማረጋገጥ መርካታ ቀናት ይፈጃል ብለዋል።
የአሜሪካ ትራንስፖርት ሚኒስትር ሲን ደፊ በተወሰኑ ወታደራዊ ስልጠናዎችና ተልእኮዎች ላይ ጥያቄ አንስተዋል።