![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/06/258-173150-whatsapp-image-2025-02-06-at-4.31.34-pm_700x400.jpeg)
በቤተ ሙከራ የተፈጠረው የካንጋሮ ጽንስ ማደግ የሚችል እና አዲስ ቴክኖሎጂ እንደሆነ ተገልጿል
የአውስትራሊያ ተመራማሪዎች የካንጋሮ ጽንስ በቤተ ሙከራ መፍጠር ቻሉ፡፡
አውስትራሊያ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የካንጋሮ ጽንስን ከተፈጥሮ ውጪ መፍጠር መቻላቸውን አስታውቀዋል፡፡
ፈጠራው የተሞከረው ልጅ በተፈጥሮ መንገድ መውለድ ላልቻሉ ሰዎች በቤተ ሙከራ አማካኝነት ልጅ እንዲወልዱ ይደረግበት የነበረውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ነው፡፡
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ይህ ፈጠራ በካንጋሮ ላይ ተሞክሮ ውጤታማ ሆኗል የተባለ ሲሆን የመጀመሪያው የካንጋሮ ጽንስ በቤተ ሙከራ አማካኝነት መፍጠር ተችሏል፡፡
ጽንሱ የተፈጠረው የወንድ እና ሴት ካንጋሮ የወንድ የዘር ፍሬ እና ሴቴ እንቁላል ጋር በቤተ ሙከራ ውስጥ እንዲዋሃድ ከተደረገ በኋላ ነውም ተብሏል፡፡
በሰው ልጆች ላይ ተሞክሮ ውጤታማ የሆነው ይህ ቴክኖሎጂ በእንስሳትም ላይ በመሞከር ላይ የቆየ ሲሆን የኩዊንስ ላንድ ዩንቨርሲቲ ተመራማሪዎች በመጨረሻም ተሳክቶላቸዋል፡፡
አዲሱ ፈጠራ በተለይም የመጥፋት አደጋ ለተደቀነባቸው እንስሳት ጥሩ መፍትሔ ሊሆን እንደሚችልም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
ሙከራው ከተጀመረ በርካታ ዓመታትን ያስቆጠረ ቢሆንም ጽንስ መፍጠር ከተቻለ በኋላ ህይወቱ እና እድገቱ እንዲቀጥል ማድረግ ፈተና ሆኖ ቆይቷል፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት ይህ ቴክኖሎጂ በኬንያ በመጥፋት ላይ ባለው አውራሪስ ላይ ተሞክሮ ውጤት ማስገኘት ችሎ ነበር፡፡
በፈረንጆቹ 2018 ላይ የመጀመሪያው የእንስሳት ጽንስ በቤተ ሙከራ መፍጠር የተቻለ ቢሆንም ተጨማሪ ምርምሮች ሲካሄድ እንደቆየም ተገልጿል፡፡