የእስራኤል ዋነኛ የጦር መሳሪያ አቅራቢዎች እነማን ናቸው?፤ የትኞቹስ ማቅረባቸውን አቆሙ?
የእስራኤል የጦር መሳሪያ በማቅረብ ጀርመን ሶስተኛ ደረጃ ይዛለች
አሜሪካ፣ የእስራኤል ጦር የመሬት ውስጥ ምሽግ የሚያፈራርሱትን ጨምሮ ከባድ መሳሪያዎችን ማቅረቧን አቁማለች
አሜሪካ፣ የእስራኤል ጦር 35ሺ ፍልስጤማውያን እንዲገደሉ ምክንያት በሆነው የስድስት ወራት ጦርነት ሲጠቀምባቸው የነበሩትን የመሬት ውስጥ ምሽግ የሚያፈራርሱትን ጨምሮ ከባድ መሳሪያዎችን ማቅረቧን አቁማለች።
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ይህን ውሳኔ ያሳለፉት የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የዋሽንግተንን ተቃውሞ ወደ ጎን በመተው ራፋን ለማጥቃት ውሳኔ ባሳለፉበት ወቅት ነው።
አሜሪካ ለመካከለኛው ምሰራቅ አጋሯ እስራኤል የጦር መሳሪያ በመቅረብ ቀዳሚ ሀገር ነች። በናዚ የአይሁድ ዘር ማጥፋት ወይም ሆሎካስት የተፈጠረውን ቁስል ለማከም በሚል ምክንያት ጭምሮ ጀርመን ለእስራኤል የጦር መሳሪያ በማቅረብ ሁለተኛ ስትሆን ጣሊያን ጀግሞ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
ሁለቱ ሀገራት ማለትም ካናዳ እና ኔዘርላንድስ ለእስራኤል የሚያቀርቧቸው የጦር መሳሪያዎች አለምአቀፍ ህጎችን በጣሰ መልኩ በጋዛ ንጹሃንን ለመግደል እና መንደሮችን ለማውደም ጥቅም ላይ ይውላሉ በሚል ስጋት አቁመዋል።
የእስራኤል ዋነኛ የጦር መሳሪያ አቅራቢዎች የሚከተሉት ናቸው።
አሜሪካ
እንደ አሜሪካ ባለስልጣናት ከሆነ ወደ እስራኤል እንዳይጫን እግድ የተጣለበት 1800 ባለ 2000 ፓውንድ (907 ኪሎግራም) ቦምብ እና 1700 ባለ 500 ፓውንድ ቦምብን ያካትታል።
ቦምቦቹ እንዳይጫኑ የተደረገው "ባለ2000 ፓውንድ ቦምቦቹ እንደ ራፋ ባሉ ብዙ ህዝብ ባለባቸው የመኖሪያ መንደሮች አደጋ ያስከትላሉ በሚል ስጋት መሆኑን ባለስልጣኑ ተናግረዋል።
አሜሪካ እና እስራኤል በ2816 ከ2018-2028 የሚቆይ ሶስተኛውን የ10 አመት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል። በዚህ ስምምነት መሰረት አሜሪካ ለወታደራዊ እርዳታ 38 ቢሊዮን ዶላር፣ ለጦር መሳሪያ መግዣ 33 ቢሊዮን ዶላር እንዲሁም እና ለሚሳይል መከላከያ ስርአት 5 በሊዮን ዶላር ትሰጣለች።
የስቶክሆልሞ አለምአቀፍ ፒስ ሪሰርች ኢንስቲቲዩት(ኤስአይፒአርአይ) ባለፈው መጋቢት ባወጣው ጥናት መሰረት እስራኤል ከ2019-2023 ድረስ 69 በመቶ የሚሆነውን ወታደራዊ ድጋፍ ያገኘችው ከአሜሪካ ነው።
እስራኤል በጣም ዘመናዊ የተባለችውን የአሜሪካን ኤፍ-35 ጆይንት ስትራይክ ፋይተር ጀትን መጠቀም ችላለች። እስራኤል ከባለፈው አመት መጨረሻ ጀምሮ 75 ባለ ኤፍ-35 የጦር ጀቶችን ለመግዛት በሂደት ላይ ስትሆን 36ቱን ተረክባለች።
ጀርመን
ጀርመን ለእስራኤል የምታደርገው እርዳታ በ2022 ከነበረው በ10 እጥፍ አድጎ በ2023 ወደ 351 ሚሊዮን ዶላር አፍ ብሏል። ነገርግን ከዚህ አመት መጀመሪያ ጀምሮ እስራኤል በጋዛ እያካሄደችው ያለው ጦርነት ከፍተኛ ትችት ማስተናገዱን ተከተሎ ጀርመን ለእስራኤል ለምታደቀርበውን የጦር መሳሪያ መጠን ቀንሳለች። በዚህ አመት 32ሺ ዩሮ ዋጋ ያላቸው የጦር መሳሪያዎች እስካሁን መላካቸውን የጀርመን የኢኮኖሚክስ ሚኒሰቴር ባለፈው ወር ገልጿል።
ጀርመን ለእስራኤል በዋናነት የምታቀርበው የአየር መከላከያ ስርአትን እና የግንኙነት መሳሪያዎችን እንደሆነ ይገለጻል።
ከ2019-23 ድረስ ጀርመን 30 በመቶ የሚሆነውን የእስራኤል ወታደራዊ እርዳታ እንደምትሸፍን ኤስአይፒአርአይ መረጃ ያሳያል።
ጣሊያን
የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ምንጭ ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው ከሶስት ትላልቅ የእስራኤል የጦር መሳሪያ አቅራቢዎች አንዷ የነበረችው ጣሊያን የጋዛ ጦርነት ከተጀመረ በኋላ መላኳን አቁማለች።
"ሁሉም ነገር ቆሟል። የመጀመረሻው ሽያጭ የተከናወነው በህዳር ወር ነበር"
የጣሊያን ህግ ጦርነት ለሚያካሄዱ እና የአለምአቀፍ ህግን ይጥሳሉ ለሚባሉ ሀገራት የጦር መሳሪያ እንዳይተላለፍ ያግዳል።
እንደ ኤስአይፒአርአይ መረጃ ከሆነ ከ2019-23 ድረስ ጣሊያን አንድ በመቶ በመቶ የሚሆነውን የእስራኤል ወታደራዊ እርዳታ ትሸፍናለች።
እንግሊዝ
እንግሊዝ ለእስራኤል ቀጥተኛ የጦር መሳሪያ ድጋፍ አታደርግም፤ ነገርግን ኩባንያዎች ለእስራኤል የጦር መሳሪያዎች የሚለው ክፍሎችን እንዲሸጡ ፍቃድ ትሰጣለች።
ባለፈው አመት ኩባንያዎች 52 ሚሊዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው የመከላከያ መሳሪያዎችን እንዲሸጡ ፍቃድ ሰጥተዋል።
ካናዳ
የካናዳ መንግስት ከጥር 8 ጀምሮ ወደ እስራኤል የጦር መሳሪያ እንዳይሄድ ማገዱን እና ይህም ኦቶዋ የጦር መሳሪያዎች በአለምአቀፍ ህግ መሰረት ጥቅም ላይ መዋላቸውን እስከምታረጋግጥ ድረስ ይቀጥላል። አለምአቀፍ የመብት ተሟጋቿቾ እንደሚሉት ከሆኑ በእስራኤል የአየር ጥቃት ውስጥ ከሞቱት ውስጥ አብዛኞቹ ንጹሃን ናቸው።
ካናዳ ሀማስ ጥቃት ከጀመረበት ባለፈው ጥቅምት ወር ወዲህ የ21 ሚሊዮን ዶላር ሽያጭ ፈጽማለች።
ኔዘርላንድስ
የደች መንግስት የኤፍ-35 የጦር ጀቶች ክፍል ከኔዘርላንድስ ማከማቻ ወደ እስራኤል ማጓጓዙን ባለፈው የካቲት ያቆመው፣ ፍርድ ቤት ጀቶቹ የሰብአዊ መብትን ለመጣስ ጥቅም ላይ ይውላሉ የሚል ውሳኔ ካሳለፈ በኋላ ነው።