ከአሜሪካ ጋር መነጋገር እንደማያዋጣ በልምድ አረጋግጠናል- የኢራኑ ካሚኒ
ትራምፕ በመጀመሪያ የስልጣን ዘመናቸው ወቅት አሜሪካን ከ2ዐ15ቱ የኢራን የኑክሌር ስምምነት አስወጥተው በድጋሚ ማዕቀብ መጣላቸው ይታወሳል
![](https://cdn.al-ain.com/images/2025/2/07/243-153958-img-20250207-143613-808_700x400.jpg)
ኢራን ከሁለት አመት ንግግር በኋላ ከአሜሪካና ሌሎች ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ ብትደርስም አሜሪካ በስምምነቱ መገዛት አልቻለችም ብለዋል
የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካሚኒ ከአሜሪካ መነጋገር የሚያዋጣ አለመሆኑን በልምድ ማረጋገጣቸውን ተናገሩ።
ካሚኒ ከአሜሪካ ጋር የሚደረግ ንግግር "አሪፍ፣ ብልሃታዊ እና ክብር የሚገባው" አለመሆኑን በልምድ ማረጋገጥ ችለናል ሲሉ መናገራቸውን ሮይተርስ ኢርና ዜና አገልግሎትን ጠቅሶ ዘግቧል።
ፕሬዝደንት ትራምፕ በኢራን ላይ ከፍተኛ የሚሉትን ዘመቻ ከከፈቱ በኋላ ከኢራን ጋር "በኑክሌር ጦር መሳሪያ ስምምነት" ጉዳይ መነጋገር እንደሚፈልጉ ባለፈው ሳምንት ገልጸዋል። ትራምፕ በመጀመሪያ የስልጣን ዘመናቸው ወቅት በ2018 አሜሪካን ቴህራን ከአለም ኃያላን ሀገራት ጋር ከደረሰችው የ2ዐ15ቱ የኑክሌር ስምምነት አስወጥተው የኢራን ኢኮኖሚን እያሽመደመደ ያለውን ማዕቀብ በድጋሚ ጥለውባታል።
ከባዶቹ እርምጃዎች ኢራን የኑክሌር ገደቡን እንድትጥስ አድርገዋታል።
"አሜሪካ ጋር የሚደረግ ድርድር አሪፍ፣ ብልህና ክብር የሚገባው አይደለም። የትኛውንም ችግራችንን አይፈታም። ምክንያቱም ከልምድ አይተናል" ሲሉ ተደምጠዋል ካሚኒ።
ኢራን ከሁለት አመት ንግግር በኋላ ከአሜሪካና ሌሎች ሀገራት ጋር ስምምነት ላይ ብትደርስም አሜሪካ በስምምነቱ መገዛት አልቻለችም ብለዋል።
"ኃላፊነት ያለበት ሰው ቀዶ ጥሎታል" ብለዋል ካሚኒ ትራምፕን በማመላከት።
አንድ ከፍተኛ የኢራን ባለስልጣን ለሮይተርስ እንደተናገሩት ኢራን አሜሪካ አለመግባባቶቹን እንድትፈታ እድል ለመስጠት ዝግጁ ናት።
"የኢራንን ደህንነት ስጋት ውስጥ የሚጥሉ ከሆነ የእነሱን ደህንነት አደጋው ውስጥ እንጥለዋለን። ማስፈራራታቸውን የሚቀጥሉ ከሆነ እኛም እንገፋበታለን።"
ትራምፕ ስላነሱት በጋዛ ያሉ ፍልስጤማውያንን ወደ ሌላ ሀገር የማዛወር ጉዳይ በተመለከተ ካሚኒ "በወረቀት ላይ ካየነው አሜሪካ የአለምን ካርታ ቀይራለች፤ ወረቀት ላይ ብቻ ነው፤ ምክንያቱም ከእውነታው ጋር አይጣጣምም" ብለዋል።