የአሜሪካን ማስጠንቀቂያ ቸል ያሉት የሰሜን ኮሪያው መሪ ሩሲያ ገቡ
የኪም የሩሲያ ጉዞ ያላስደሳት አማሪካ፣ ሰሜን ኮሪያ ከሩሲያ ጋር በጦር መሳሪያ ጉዳይ እንዳትስማማ እያሰጠነቀቀች ባለችበት ወቅት ነው ኪም ሩሲያ የገቡት
የኪም የሩሲያ ጉብኝት የማይቀር እንደሆነ ሲናገሩ የነበሩት የአሜሪካ ባለስልጣናት በሰሜን ኮሪያ እና ሩሲያ መካከል ያለው የጦር መሳሪያ ንግግር እየጠነከረ መምጣቱን ገልጸዋል
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሩሲያ የገቡት በጦር መሳሪያ ዙሪያ ለመነጋገር ነው ተብሏል።
ክሬሚሊን እንደገለጸው ኪም ጆንግ ኡን ከፕሬዝደንት ፑቲን ጋር ዝርዝር ውይይት ያደርጋሉ።
የኪም የሩሲያ ጉዞ ያላስደሳት አሜሪካ፣ ሰሜን ኮሪያ ከሩሲያ ጋር በጦር መሳሪያ ጉዳይ እንዳትስማማ እያሰጠነቀቀች ባለችበት ወቅት ነው ኪም ሩሲያ የገቡት።
ኪም የሀገሪቱን የወታደራዊ ኢንዱስትሪ መሪዎች፣ ወታደራዊ ባለስልጣናት እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስከትለው በግል ባቡራቸው ባለፈው ቅዳሜ እለት ከፒዮንግያንግ መነሳታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ኪም ጆንግ ኡንን ያሳፈረችው መርከብ ሰሜን ኮሪያን ከሩሲያ በሚያገናኘው የካሳን ባቡር ጣቢያ መድረሷ ተገልጿል።
የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ እንደገለጹት ኪም ሩሲያ የደረሱት ማክሰኞ ጠዋት ነው ብለው ያምናሉ።
ብዙም የውጭ ጉዞ የማያዘወትሩት ኪም በስልጣን ዘመናቸው ወደ ሰባት ጊዜ ብቻ ነው የውጭ ጉብኝት ያደረጉት።
ክሬሚሊን የኪም ጉብኝቱ ዘርፈ ብዙ ሊሆን እንደሚችል ተናግሯል።
የክሬሚሊን ቃል አቀባይ ዲሜትሪ ፔስኮቭ "በሁለቱ ሀገራት መካከል ንግግሮች ይኖራሉ፣ ከዚያ በኋላ አስፈላጊ ከሆነ ሁለቱ መሪዎቹ የአንድ ለአንድ ንግግራቸውን ይቀጥላሉ።"
የኪም የሩሲያ ጉብኝት የማይቀር እንደሆነ ሲናገሩ የነበሩት የአሜሪካ ባለስልጣናት በሰሜን ኮሪያ እና ሩሲያ መካከል ያለው የጦር መሳሪያ ንግግር እየጠነከረ መምጣቱን ገልጸዋል። እንደባለስልጣናቱ ከሆነ ኪም እና ፑቲን ሩሲያ በዩክሬን ለምታደርገው ጦርነት የጦር መሳሪያ በምታገኝበት ጉዳይ ይመክራሉ ብለዋል።
ፒዮኖያንግ እና ሞስኮ ግን ሰሜን ኮሪያ ለሩሲያ የጦር መሳሪያ አቅርባለች የሚለውን ክስ አስተባብለዋል።