የሰሜን አፍሪካ አረንጋዴ ሀይድሮጅን ወደ ውጭ የመላክ እቅድ
አውሮፖ ዋና የገበያ ቦታ እንደሚሆን ሪፖርቱ ጠቅሷል
ሰሜን አፍሪካ በፈረንጆቹ 2050 አረንጓዴ ሀይድሮጅን ወደ ውጭ በመላክ አለምን የሚያስደምም እቅድ ነድፏል
ሰሜን አፍሪካ በፈረንጆቹ 2050 አረንጓዴ ሀይድሮጅን ወደ ውጭ በመላክ አለምን የሚያስደምም እቅድ ነድፏል።
እንደ ደሎይቴ ሪፖርት ከሆነ ሰሜን አፍሪካ ከፍተኛ የአረንጋዴ ሀይድሮጅን ላኪ በመሆን 100 ቢሊዮን ዶላር ትርፍ ሊያገኝ ይችላል።
አውሮፖ ዋና የገበያ ቦታ እንደሚሆን ሪፖርቱ ጠቅሷል። እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በፈረንጆቹ 2050 ዋናዋና የሀይድሮጅን አምራቾች የሚሆኑት ሰሜን አፍሪካ 110 ቢሊዮን ዶላር፣ ሰሜን አሜሪካ 63 ቢሊዮን ዶላር፣ አውስትራሊያ 39 ቢሊዮን ዶላር እና መካከለኛው ምስራቅ 20 ቢሊዮን ያገኛሉ።
ሪፖርቱ እንደገለጸው አረንጓዴ ሀይድሮጅን በ2050 1.4 ትሪሊየን ዶላር የሚገመት ዋጋ ይኖረዋል።
በአሁኑ ወቅት በአለም ከሚመረተው የሀይድሮጅን ምርት አረንጓዴ የሆነው ከአንድ በመቶ በታች ነው። ነገርግን የአየርንብረት ለውጥ ያስከተለው ቀውስ እና የመንግስት እና የግል ኢንቨስትመንት መኖር በዚህ ዘርፍ ፈጣን ኢንቨስትመንት እንዲኖር አስተዋጽኦ አድርጓል።
የሀይድሮጆን አማካሪ የተባለ ቡድን በዓለም ላይ ከአንድ ሺ በላይ የሀይድሮጅን ኢንቨስትመንት እየተካሄደ ነው ብሏል።
ሪፖርቱ እንደገለጸው ከጸሀይ ብርሃን እና ከንፋስ ኃይል የሚገኘው ሀይድሮጅን ገበያ ብቅ ማለት በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ያሉ ኢንዱስትሪዎች አካታች እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። ለምሳል በደቡባዊ የአለም ክፍል ያሉ የብረት ፋብሪካዎች ከሰል መጠቀማቸውን እንዲያቆሙ ይዳቸዋል ይላል ሪፖርቱ።