ኪም ጆንግ ኡን ጦራቸው ለእውነተኛ ጦርነት ዝግጅት እንዲያደርግ ትእዛዝ አስተላለፉ
የሰሜን ኮሪያ መሪ የጦር መሳሪያ ሙከራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አስተላለፍዋል
ኪም ጆንግ ኡን ጦራው ለሁለት ስትራቴጂካዊ አላማዎች ዝግጅት እንዲያደርግም ጥር አስተላልፈዋል
የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጦራቸው ለ'በእውነተኛ ጦርነት ልምምድ እንዲያደርጉ ትእዛዝ ማስተላለፋቸው ተነግሯል።
መሪው ኪም ጆንግ ኡን የሀገሪቱ ጦር የሚያደርገውን ወታደራዊ ልምምድ እና ሙከራዎች አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ማለታውን ኬ.ሲ.ኤን.ኤ ዘግቧል።
የሀገሪቱ የከባድ መሰሳሪያ ዩኒት ለሁለት ከፍተኛ ተልእኮዎች መዘጋጀት እንዳለበትም ነው መሪው በመልእክታቸው ያስታወቁት።
- የሰሜን ኮሪያው መሪ የጠላትን ጥቃት ለመከላከል ሁሌም ዝግጁ መሆን ያስፈልጋል አሉ
- ሰሜን ኮሪያ ማንኛውም የአሜሪካ ወታደራዊ እንቅቃሴ “የጦርነት አዋጅ” አድርጋ እንደምትቆጥር አሳሰበች
የመጀመሪያው ተልእኮ ጦርነትን ቀድሞ ተከላክሎ ማስቀረት ሲሆን፤ ሁለተኛው ተልእኮ ደግሞ ጦርነት ውስጥ የበላይት ለመውሰድ እንደሆነም አስታውቀዋል ነው የተባለው።
ሰሜን ኮሪያ እያደረገች ያለውን የሚሳዔል ሙከራዎች አጠናክራ ቀጥላች የተባለ ሲሆን፤ ባሳለፍነው ሐሙስ የአጭር ርቀት የባላስቲክ ኪሳዔሎችን ማስወንጨፏን ደቡብ ኮሪያ አስታውቃለች።
ሰሜን ኮሪያ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዋሽንግተን አጋሮቿ እያደረጉት ያለውን የጋራ ወታደራዊ ልምምድ የቀጠናውን ሁኔታ ወደ “ቀይ መስመር” እንደወሰደው በተለያዩ ጊዜያት ስትናገር መቆየቷ ይታወሳል።
በኮሪያ ልሳነ ምድር ለተፈጠረው ውጥረት አሜሪካን ተጠያቂ የምታደርገው ሰሜን ኮሪያ ከአሁን በኋላ የሚደረግ ማንኛውም የዋሽንግተን ወታደራዊ እንቅቃሴ “የጦርነት አዋጅ” አድርጋ እንደምትቆጥረውም አሳስባለች።