ሰሜን ኮሪያ ማንኛውም የአሜሪካ ወታደራዊ እንቅቃሴ “የጦርነት አዋጅ” አድርጋ እንደምትቆጥር አሳሰበች
ሰሜን ኮሪያ “ኃላፊነት የጎደለው ነው” ያለውችን የአሜሪካና የደቡብ ኮሪያ እንቅስቀሴ አውግዛለች
“ኃይለኛዋ” የፕሬዳንት ኪም እህት፤ የአሜሪካና የደቡብ ኮሪያ ከድርጊታቸው ካልተቆጠቡ በኮሪያ ልሳነ ምድር ጦርነት ይነሳል ብለዋል
በኮሪያ ልሳነ ምድር ለተፈጠረው ውጥረት አሜሪካን ተጠያቂ የምታደርገው ሰሜን ኮሪያ ከአሁን በኋላ የሚደረግ ማንኛውም የዋሽንግተን ወታደራዊ እንቅቃሴ “የጦርነት አዋጅ” አድርጋ እንደምትቆጥረው አሳስባለች።
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን እህት ኪም ዮ ጆንግ በሰጡት መግለጫ "ሰሜን ኮሪያ ስትራቴጅካዊ የጦር መሳሪያ ሙከራዋን በሚቃረን መልኩ በአሜሪካ በኩል የሚደረግ ማንኛውንም ወታደራዊ እርምጃ እንደ ጦርነት ማወጅ ትቆጥራለች" ሲሉ ተናግረዋል።
ኃይለኛዋ የኪም እህት ንግግራቸው በንግግራቸው አክለውም “ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ብንሰጥም አሜሪካ ሆን ብላ ሁኔታውን ማባባሱን ቀጥላበታለች” ሲሉ ተደምጠዋል።
በተየያዘ የሰሜን ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “በአሜሪካ እና በደቡብ ኮሪያ መካከል ሚደራገውና B-52 ስትራቴጂካዊ ቦምቦችን ያካተተው የጋራ ልምምድ ” ማውገዙን የኮሪያ ማዕከላዊ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።
- የሰሜን ኮሪያው መሪ እህት አሜሪካን በሚሳኤል አስጠነቀቁ
- ሰሜን ኮሪያ አህጉር አቋራጭ ባላስቲክ ሚሳይል ማስወንጨፏን ተከትሎ አሜሪካና ደቡብ ኮሪያ የጋራ የአየር ልምምድ አደረጉ
አሜሪካ ከደቡብ ኮሪያ ጋር በምታደርገው የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ሁኔታውን ለማባባስ ሆን ብላ እየሰራች ነው ሲልም ወቅሷል ሚኒስቴሩ።
ሰሜን ኮሪያ የዋስንግተን እና ሴኡልን ጥምረት ብታወግዝም ሀገራቱ አሁንም የጋራ ወታደራዊ ልምምዳቸው አጠናክረው እንደቀጠሉበት ነው።
የደቡብ ኮሪያ መከላከያ ሚኒስቴር ሰኞ እለት ያሰራጨው ቪዲዮ የሚያሳየውም ሁለቱ ሀገራት የአየር ሃይል ተዋጊዎች በኮሪያ ልሳን ምድር ልምምዶችን ሲያደርጉ ነው።
ሀገራቱ ልምምዱን የሚያደርጉት ከሰሜን ኮሪያ ሊቃጣባቸው የሚችል የኒውክሌር አደጋ ለመከላከል መሆኑ ቢገልጹም፤ ፒዮንጊያንግ ግን “ግዛቴን ለመውረር” ነው ስትል ትደመጣለች።
ሁኔታው ያሳሰበው የሰሜን ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር "በቅርቡ የተካሄደው የጋራ የአየር ልምምዶች በግልጽ እንደሚያሳየው አሜሪካ በሰሜን ኮሪያ ላይ የኒውክሌር ጦር መሳሪያን ለመጠቀም እቅድ እንዳላት አመላካች ነው" ሲል ያለውን ስጋት ገልጿል።
"በኮሪያ ልሳነ ምድር ያለውን ሁኔታ ወደማይታወቅ ሁኔታ በመግፋት አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ እያሳዩት ባለው ኃላፊነት የጎደለው እና አስደንጋጭ የኃይል ትርኢት በጣም አዝነናል" ያኩት ደግሞ ኃይለኛዋ ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን እህት ኪም ዮ ጆንግ ናቸው።
በኮሪያ ልሳነ ምድር ላይ ሰላምና መረጋጋትን የሚያናጉ ወታደራዊ እርምጃዎች በአስቸኳይ እንዲቆሙ እንጠይቃለን ያሉት ኪም ዮ ጆንግ፤ ያ’ ካልሆነ በኮሪያ ልሳነ ምድር ላይ ከባድ ግጭት ላለመቀነሱ ምንም ዋስትና የለም ሲሉም አስጠንቅቀዋል።
ሴኡል እና ዋሽንግተን አርብ ዕለት እንዳስታወቁት ከሰሜን ኮሪያ ሊቃጣ የሚችለውን የላቀ የኒውክሌር እና የሚሳኤል ስጋት ለመከላከል በሚል በዚህ ወር መጨረሻ የጋራ የጸደይ ወታደራዊ ልምምድ ለመጀመር ማቀዳቸውን ማስታወቃቸው አይዘነጋም።
ሀገራቱ ልምምዱን የሚከናወኑት ከመጋቢት 13 እስከ 23 ባለው ጊዜ ውስጥ ሲሆን፤ ይህም የመከላከያ አቅምን ለማጠናከር በማሰብ በጋራ ማዘዣ ማእከል ውስጥ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ነው ተብሏል።
አሜሪካ እና ደብቡ ኮሪያ ከሰሜን ኮሪያ ጋር ያላቸውን ውጥረት ማርገብ ካልቻሉ ቀጠናው ወደለየለት ቀውስ አንዳይገባ ሚለው ጉዳይ አሁንም በርካታ የፖለቲካ ሳይንስ ልሂቃን በስጋት የሚያነሱት ጉዳይ ሆኖ እንደቀጠለ ነው።