“የሰሜን ኮሪያ ግብ የዓለም ኃይለኛ የኒውክሌር ኃይል ባለቤት መሆን ነው- ኪም ጆንግ ኡን
ኪም ጆንግ ኡን በህዋሶንግ-17 አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል ሙከራ ላይ ለተሳተፉ ሳይንቲስቶችና ወታደሮች እውቅና ሰጥተዋል
“ሁዋሶንግ-17” አሜሪከን መምታት የሚችል አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤል መሆኑን ኪም ጆንግ ኡን አስታውቀዋል
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የሀገራቸው ትልቁ ግብ የዓለም ኃይለኛ የኒውክሌር ኃይል ባለቤት መሆን እንደሆነ ገለጹ።
ሰሜን ኮሪያ በህዋሶንግ-17 አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል ሙከራ ላይ ለተሳተፉ ሳይንቲስቶችና ወታደሮች እውቅና እና የማእረግ እድገት መስጠታቸውን የኮሪያ ሴንተራል ኒውስ ኤጀንሲ ዘግቧል።
ኪም ጆንግ ኡን በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግርሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ሃይል እየገነባች ያለችው የሀገሪቱን እና የህዝቡን ክብር እና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ነው ብለዋል።
የሰሜን ኮሪያ "የመጨረሻው ግብ በዓለም ላይ እጅግ ኃያል የሆነ የስትራቴጂክ መገንባት ነው” ያሉት ኪም ጆን ኡን “ይህም በክፍለ ዘመኑ ታይቶ የማይታወቅ ፍፁም ኃይል" ይሆና ሲሉም ተናግረዋል።
መሪው ኪም ጆንግ ኡን አክለውም ህዋሶንግ-17 አህጉር አቋራጭ ሚሳኤል የዓለማችን ኃይለኛው ስትራቴጂክ የጦር መሳሪያ ነው ያሉ ሲሆን፤ አሜሪካን መምታት አቅም ያለው መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ህዋሶንግ-17 አህጉር አቋራጭ የባላስቲክ ሚሳዔል የተሳካ ሙከራ ሰሜን ኮሪያ የዓለም ጠንካራ ሰራዊት ለመገንባት መቻሏን አሳይቷል ብለዋል።
ሰሜን ኮሪያ ባሳለፍነው ሳምንት ህዋሶንግ-17 አህጉር አቋራጭ የባላስቲክ ሚሳዔል ሙከራ አድርጋ እንደነበረ ይታወሳል።
ፒዮንያንግ አሜሪካ መድረስ የሚችልው ባለስቲክ ሚሳኤል ወደ ጃፓን ያስወነጨፈች ሲሆን፤ የባለስቲክ ሚሳኤሉ 1 ሺህ ኪሎሜትሮችን መጓዙ ተነግሯል።
ይህም ከተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት እና ከአሜሪካ ከፍተኛ ውግዘትን አስከትሎባታል።