የሰሜን ኮሪያው መሪ በአባታቸውን የሙት አመት መታሰቢያ ስነ-ስርአት ላይ አልተገኙም ተባለ
ፕሬዝዳንት ኪም ያልተኙት 2023 እቅዶች ማውጣት ላይ ተጠምደው ሊሆን ይችላል ተብሏል
የኪም ጆንግ ኡን በስነ-ስርአቱ ላይ አለመገኘት ያልተለመደ መሆኑ እየተነገረ ነው
የኮሪያው መሪ ኪም ጁንግ ኡን በአባታቸውን የ11ኛ ሙት አመት መታሰቢያ ስነ-ስርአት ላይ አለመገነኘታቸው የሀገሪቱ ሚዲያ ሴንትራል ኒውስ ኤጀንሲ (ኬሲኤንኤ) ዘግቧል፡፡
ይሁን እንጅ በትናንትናው እለት ኪም ጆንግ-ኢልን ለመዘከር በተካሄደው ስነ-ስርአቱ ላይ የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናትና የገዢው ፓርቲ አባላት ፒዮንጊያንግ በሚገኘው የኩምስሱያን ቤተ መንግስት ላይ መገኘታቸውን ተገልጿል፡፡
ኬሲኤንኤ የለቀቀው ምስል እንደሚሳየውም ፤ በስነ-ስርአቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪም ቶክ ኡን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቾይ ሶን ሁዋይ እና የገዢው ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ ዋና ጸሃፊ ፓክ ጆንግ-ቾን እና ሌሎች ባለስልጣናት ቢገኙም ፕሬዝዳንት ኪም ጆን ኡን አልታዩም፡፡
በዚህም ለሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት ኪም ጆንግ ኡን የአበባ ጉንጉን ማስቀመጫ የሚሆን ስፍራ ክፍት እንደተደረገ ተዘግቧል፡፡
ላላፉት አስር አመታት በተካሄዱ መታሰቢያ ስነ-ስርአቶች ላይ ይገኑ ነበሩ ኪም ጆንግ ኡን እና እህታቸው ኪም ዮ ጆንግ በቦታው ላይ አለመገኘት አዲስ ቢሆንም በጣም አስፈላጊ በሆኑ ስራዎች ላይ ሳይጠመዱ እንዳልቀረ እየተነገረ ነው፡፡
በደቡብ ኮሪያ ኢንሰቲትዩት ፎር ናሽናል ዩኒፊኬሽን ተመራማሪ የሆኑት ሆንግ ሚን፤ ኪም በአባታቸው መታሰቢያ ላይ ያለልተገኙት የ2023 እቅዶችን ለማውጣት ጊዜ አስፈልጓቸው ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል የኪም አለመገኘት ሰሜን ኮሪያ የጃፓን ባህር ተብሎ ወደ ሚጠራውን የውሃ አካል ላይ ካስወነጨፈቻቸው ሁለት ሚሳይሎች ጋር እየተያያዘ ይገኛል፡፡
የደቡብ ኮሪያ ጦር እንደገለጸው ከሆነ ፒዮንጊያንግ ያስቀነጨፈቻቸው ሁለት ሚሳይሎች መካከለኛ ሬንጅና ወደ 500 ኪሎ ሜትር ርቀት ሊምዘገዘጉ የሚችሉ ናቸው፡፡