ሰሜን ኮሪያ የዓለም ትልቁ የኒውክሌር ኃይል ባለቤት ትሆናለች - ኪም ጆንግ ኡን
ፒዮንጊያንግ የሃዋሶንግ-17 አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤል ሙከራ አድርጋለች
ኪም ከአሜሪካ በኩል ሊቃጣ የሚችል የኒውክሌር አደጋ ለመከላከል ቃል መግባታቸው ይታወሳል
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሀገራቸው ዓለም ትልቁ የኒውክሌር ሀይል ባለቤት ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ተናገሩ።
ኪም ጆንግ ኡን ይህን ያሉት አዲሱን የሃዋሶንግ-17 አህጉር አቀፍ ባሊስቲክ ሚሳኤል ሙከራ ከተመለከቱና የሚሳኤል ማስወንጨፉ ላይ የተሳተፉትን በደርዘን የሚቆጠሩ የጦር መኮንኖችን የማበራተቻ እድገት በሰጡበት ወቅት መሆኑን ኬሲኤንኤ ዘግቧል።
ኪም ባለፈው ሳምንት ከአሜሪካ በኩል ሊቃጣ የሚችለውን የኒውክሌር አደጋ በኒውክሌር ጦር መሳሪያ ለመከላከል ቃል መግባታቸው ይታወሳል።
የኪም ንግግር በቻይና መሪ ዢ ጂንፒንግ በደብዳቤ ካቀረበቡላቸው የትብብር ጥሪ ከሰዓታት በኋላ የተደረገ መሆኑ አነጋጋሪ ሆኗል።
የቻይናው ፕሬዝዳንት በደብዳቤያቸው ለሰሜን ኮሪያውን መሪ በዓለም ላይ "ሰላምን ለማስፈን" በትብብር እንስራ የሚል ጥያቄ አቅርበውላቸዋል።
በጥቅምት ወር የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ዋና ጸሃፊ ሆነው የተመረጡት ዢ በወቅቱ የእንኳን ደስ ያለዎት ደብዳቤ ለጻፉላቸው የኮሪያው መሪ ኪም በጻፉት ደብዳቤ “ዓለም፣ ዘመን እና ታሪክ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየተለወጡ ነው” ስለዚህም በትብብር መስራቱ የተሻለ አማራጭ ነው ብለዋል።
"ይህን አዲስ ሁኔታ በመጋፈጥ እኔ (ዢ ጂንፒንግ) በቀጠናው እና በተቀረው ዓለም ሰላም፣ መረጋጋት፣ ልማት እና ብልጽግናን ለማፋጠን ከእናንተ ጋር አወንታዊ አስተዋጽኦ ለማድረግ ፈቃደኛ ነኝ" ሲሉም ጽፏል ፕሬዝዳንቱ።
ቻይና በኒውክሌር እና ሚሳኤል ፕሮግራሞቿ ምክንያት ተመድ በጣለው ከባድ ማዕቀብ ተጽእኖ ኢኮኖሚዋ የሚጎዳው እየደቀቀ ያለችውን ሰሜን ኮሪያ ዋነኛ አጋር መሆኗ ይታወቃል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ሰኞ ካደረገው ስብሰባ በኋላ ቻይና እና ሩሲያ የፒዮንግያንግ አህጉር አቋራጭ የባለስቲክ ሚሳኤልን ያወገዙትን አሜሪካ ፣ህንድ፣ፈረንሳይ እና ብሪታንያ ጨምሮ 13ቱ የምክር ቤት አባላትን ለመቀላቀል ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውንም አይዘነጋም።
ባለፈው ሳምንት በባሊ ከተካሄደው የቡድን-20 መሪዎች ስብሰባ ጎን ለጎን የአሜሪካው ፕረሬዝዳንት ጆ-ባይደን የቻይናው አቻቸውን ሰሜን ኮሪያ አዲስ የኒውክሌር ሙከራ እንዳታደርግ ኪምን እንዲያስምኑ ተማጽኗቸው እንደነበርም የሚታወስ ነው።