የሰሜን ኮሪያውን መሪ በስብሰባ መካከል ያስለቀሰው ጉዳይ ምንድን ነው?
ኪም ጆንግ ኡን በፒዮንግያንግ በተካሄደው "5ኛው የእናቶች ብሄራዊ ኮንፈረንስ" ላይ ሲያነቡ ታይተዋል
ኪም ጆንግ ኡን የሀገራቸው ሴቶች ብዙ ልጆች እንዲወልዱ አሳስበዋል
የሰሜን ኮሪያውን መሪ ኪም ጆንግ ኡን በፒዮንግ ያንግ ከእናቶ ጋር በተካሄደ ስብሰባ ላይ ሲያነቡ መታየታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።
ኪም ጆንግ ኡን በፒዮንግያንግ በተካሄደው "5ኛው የእናቶች ብሄራዊ ኮንፈረንስ" ላይ ሲያነቡ ታይተዋል የተባለ ሲሆን፤ ምክንያ ደግሞ በሀገሪቱ የወሊድ ምጣኔ ችግር ውስጥ በመግባቱ ነው ተብሏል።
የሰሜን ኮሪያውን መሪ ኪም ጆንግን ያስለቀሳቸው ጉዳይም በሀገሪቱ እያሽቆለቆለ የመጣው የወሊድ ምጣኔ ነው የተባለ ሲሆን፤ የወሊድ ምጣኔ መጠን በእጅጉን መቀነሱን የሚያሳይ ሪፖርት ሲመለከቱ ማልቀሳቸውም ነው የተነገረው።
ኪም ጆንግ ኡን ከእናቶች ጋር በነበራቸው ስብሰባ ላይም ዝቅተኛ የወሊድ ምጣኔን ለመቅረፍ በተያዘው ስትራቴጂ መሰረት የሀገራቸው ሴቶች ብዙ ልጆች እንዲወልዱ አሳስበዋል።
"የወሊድ መጠን መቀነስን ማቆም እና ጥራት ያለው የህጻናት እንክብካቤ እና ትምህርት መስጠት የቤተሰባችን ጉዳይ ነው” ያሉት ኪም ጆንግ ኡን “ከእናቶቻችን ጋር ልንፈታው የሚገባን ጉዳይ ነው” ሲሉም ተናግረዋል።
ከሰሜን ኮሪያ የወጡ መረጃዎች እንደሚያመላክቱት ከሆነ በገንዘብ ጉዳይ፣ በትምህርት ተደራሽነት እና በስራ እድል ሳቢያ አብዛኛው ደቡብ ኮሪያውያን ከአንድ ልጅ በላይ የመውለድ ፍላጎት የላቸውም።
የሰሜን ኮሪያ መንግስት ሚዲያ እንደዘገበው ሀገሪቱ ሶስት እና ከዚያ በላይ ልጆች ላሏቸው ቤተሰቦች ማበረታቻ መስጠት ጀምራለች።
ማበረታቻዎቹ ነፃ መኖሪያ ቤት፣ የመንግስት ድጎማ፣ ነፃ ምግብ፣ መድሃኒት እና የቤት እቃዎች እንዲሁም ለህፃናት የትምህርት ጥቅማጥቅሞች ያካተቱ ናቸው።