ጆንግ የደቡብ ኮሪያውን መሪ ዩዎን ሱክ ዩዎልን "አፍህን ዝጋ" ያሉበት መግለጫ ከአወዛጋቢዎቹ መግለጫቸው ውስጥ አንዱ እና የቅርብ ጊዜው ነው
ጥቂቶች አወዛጋቢ መግለጫ በመስጠት የምትታወቀውን የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡንን እህት ኪም ዮ ጆንግን የዓለም ኃያሏ ሴት ነች ይሏታል።
ዮንግ የደቡብ ኮሪያውን መሪ ዩዎን ሱክ ዩዎልን "አፍህን ዝጋ" ያሉበት መግለጫ ከአወዛጋቢዎቹ መግለጫቸው ውስጥ አንዱ እና የቅርብ ጊዜው ነው።
ጥቂቶች ጆንግ አደገኛ ሴት እንደሆነች ይናገራሉ።ሌሎች ደግሞ ደግሞ ከዚህም አልፈው እንዲህ አይነት ኃይል እና አምባገንነት የተላበሰች ሴት በታሪክ አልታየችም ይላሉ።
ሴትዮዋን ኃያል እንድትላበስ ያደረጋት ደግሞ በኑክሌር ስለምታስፈራራ ነው ሲል ዘግቧል የእንግሊዙ ዴይሊ ሜል ጋዜጣ።
ደቡብ ኮሪያዊው ጸኃፊ ሶንግ ዩን ሊ "አህት- ኪም ዮ ዮንግ በዓለም አደገኛ ሴት" በሚል ርዕስ በጻፈው መጽሀፉ በሰሜን ኮሪያ አስተዳደር ውስጥ የጆንግን ኃያል ሆኖ መውጣት ከትቧል።
ጸኃፊው የሴትዮዋ ኃያልነት የኪም ጆንግ ኡን ቤተሰብ ከመሆኗ የሚመነጭ ነው ብሏል።
ሊ እንደጻፈው የኪም ቤተሰቦች የሰሜን ኮሪያ ህዝብ በስልጣናቸው ላይ እንዳይነሳ እና እንዲፈራ ሶስት ሚጥሮችን ደብቀዋል።
እንደ ጸኃፊው ከሆነ የመጀመሪያው ህዝብ እንዳያውቅ የሚፈልጉት የጆንግ እናት እና ኪም ጆንግ ኡን ጃፖን ውስጥ መወለዳቸውን ነው።
ሁለተኛው ሚስጥር ደግሞ በፈረንጆቹ 1998 ከአክስታቸው አንዷ መክዳቷን እና ወደ አሜሪካ መሄዷን ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ የኪም እናት የቤተክርስቲያን አገልጋይ መሆናቸውን ነው ይላል ጸኃፊው።
ጆንግ ከአባታቸው ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በአደባባይ የታዩት በፈረንጆቹ በ2011 ነበር።