የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ፑቲን በሰጧቸው ቅንጡ መኪና ሲጓዙ ታዩ
ባለፈው መስከረም ወር ኪም በሩሲያ ባደረጉት ጉብኝት ከፑቲን ጋር ከመከሩ ወዲህ በፒዮንግያንግ እና በሞስኮ መካከል ያለው ግንኙነት ተጠናክሯል
የሰሜን ኮሪ መሪ ኪም ጆንግ ኡን የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በሰጧቸው ቅንጡ መኪና ሲጓዙ በትናንትናው እለት በአደባባይ መታየታቸው ተገልጿል
የሰሜን ኮሪ መሪ ኪም ጆንግ ኡን የሩሲያ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በሰጧቸው ቅንጡ መኪና ሲጓዙ በትናንትናው እለት በአደባባይ መታየታቸው ተገልጿል።
ባለፈው መስከረም ወር ኪም በሩሲያ ባደረጉት ጉብኝት ከፑቲን ጋር ከመከሩ ወዲህ በፒዮንግያንግ እና በሞስኮ መካከል ያለው ግንኙነት ተጠናክሯል።
ሰሜን ኮሪያ፣ ሩሲያ በዩክሬን ለምታደርገው ጦርነት የጦር መሳሪያ ድጋፍ አድርጋለች የሚለውን ክስ ሁለቱም አስተባብዋል።
ሮይተርስ የሰሜን ኮሪያውን ኬሲኤንን ጠቅሶ እንደዘገበው የኪም እህት ኪም ዮ ጆንግ፣ የኪም በሩሲያ ሰራሻ አውረስ መኪና ላይ መጓዛቸው "የሩሲያ እና ሰሜን ኮሪያ ግንኙነት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያሳይ ነው"ብለዋል።
ኪም ጆንግ ኡን በትንናትናው እለት በሀገሪቱ ጦር ያደረገውን ወታደራዊ ልምምድ መቃኘታቸውንም ዘገባው ጠቅሷል።
ሰሜን ኮሪያ ይህን ልምምድ ያደረገች ተቀናቃኟ ደቡብ ኮሪያ እና አጋሯ አሜሪካ ያደረጉት አመታዊ ወታደራዊ ልምምድ ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ነው።
ኪም "እውነታውን ያገናዘበ ልምምድ ማድረግ ወታደሮች ለትክክለኛ የውጊያ ብቃት ያበቃል" ብለዋል።
አሜሪካ እና ደቡብ ኮሪያ ያደረጉት ወታደራዊ ልምምድ ሰሜን ኮሪያ ባለፈው ህዳር ወር የ2018ቱን ግጭት የማርገብ ስምምነት ከሰረዘች በኋላ የመጀመሪያቸው ነው።
ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ የሚያደርጉት ተደጋጋሚ ወታደራዊ ልምምድ እንደሚያሰጋት የምትገልጸው ሰሜን ኮሪያ ራሷን እንደምትከላከል ትገልጻለች።