አሜሪካ ኪም ጆንግ ኡን 7ኛውን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራ ለማድረግ "በዝግጅት ላይ" ናቸው አለች
አሜሪካ እና አጋሮቿ ስጋታቸው ቢገልጹም በፒዮንግያንግ በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም
ሰሜን ኮሪያ ላለፉት አምስት ዓመታት የኒውክሌር ሙከራ ሳታደርግ መቆይቷ ይታወቃል
ሰሜን ኮሪያ “በየትኛውም ጊዜና አጋጠሚ” ሰባተኛውን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራ ልታደርግ እንደምትችል አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ ዲፕሎማት አስጠነቀቁ፡፡
ከሰሜን ኮሪያ ጋር የተፈጠረውን አለመግባባት የመቆጣጠር ሃላፊነት የተሰጣቸው ከፍተኛ የአሜሪካ ዲፕሎማት ሱንግ ኪም ማስጠንቀቂያውን የሰጡት፤ ፒዮንግያን ባሳለፍነው እሁድ ስምንት የባላስቲክ ሚሳዔሎች የማስወንጨፍ ሙከራ ማድረጓን ተከትሎ ነው፡፡
ሙከራው ተከትሎ ማንኛውም የኒውክሌር ሙከራ “ፈጣንና ጠንከር ያለ ምላሽ ያስፍለገዋል ” ሲሉ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስርያ ቤት ሚኒስቴት ሚኒስትር ዴኤታ ዌንዲ ሸርማን ለጋዜጠኞች መናገራቸው ይታወሳል፡፡
ሰሜን ኮሪያ ላለፉት አምስት ዓመታት የኒውክሌር ሙከራ ሳታደርግ መቆይቷ ይታወቃል፡፡
ይሁን እንጂ አሁን በኮሪያ ልሳነ ምድር የነገሰውን ውጥረት ሀገሪቱ የኒውክሌር ሙከራ እስከማድረግ ልትደርስ እንደምትችል ተሰግቷል፡፡
በኢንዶኖዝያ፤ ጃካርታ ሆነው መግለጫ የሰጡት ኪም እንደሚሉት ፤ ሰሜን ኮሪያ በዚህ አመት ብቻ ያልተጠበቁ የሚሳዔል ስታስወነጭፍ ቆይታለች ብለዋል፡፡
ፒዮንግያንግ በዚህ ዓመት ብቻ 31 የሚሳዔል ሙከራዎች አስቀንጭፋለች፡፡
ኪም እንደሚሉት ከሆነ፤ ኪም ጆንግ ኡን ሰባተኛውን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራ ለማድረግ "በዝግጅት ላይ" ናቸው።
የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ሙከራው መች ሊሆን ይችላል የሚል ጥያቄ ከጋዜጠኞች የቀረበላቸው ኪም “በየትኛውም ጊዜ ሊሆን ይችላል” የሚል ምልሽ ሰጥተዋል፡፡
ከደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን ባለስልጣናት ጋር ግንኙነት በማድረግ ላይ ያሉት ዌንዲ ሸርማን በበኩላቸው፤ እንዲዘህ አይነት ሙከራዎች “ በጸጥታው ምክር ቤት የተደረሱ ስምምነቶች የሚጥሱ ናቸው ”ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
“ለጉዳዩ ደቡብ ኮሪያ፡ አሜሪካ እና ጃፓን ብቻ ሳይሆኑ መላው ዓለም ምላሽ እንደሚሰጥበት አምናለሁ” ሲሉም አክለዋል የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታዋ ዌንዲ ሸርማን።
አሜሪካ እና አጋሮቿ ስጋታቸው በመግለጽ ላይ ቢሆኑም፤ ሰሜን ኮሪያ በጉዳ ላይ ያለችው ነገር የለም፡፡
አሜሪካ ያላትን ስጋት ብትገልጽም ጉዳዩን በዶፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት “ ያለም ምንም ቅድመ ሁኔታ ለመነጋገር” ዝግጁ መሆኗ ከፍተኛ ዲፐልማቱ ኪም አስታውቀዋል፡፡
የአሜሪካን ዝግጁነት በተመለከተ የፕዮንግያንግ ሰዎች እንዲያውቁት መደረጉም ተናግረዋል፡