ሰሜን ኮሪያ ሚሳዔሎቹ በአየር መከላከያ ስርዓት ለመምታት አዳጋች የሚያደርግ ቴክኖሎጂ ተጠቅማለች
ሰሜን ኮሪያ አንድ አህጉር አቋራጭ ባላስቲክ ሚሳዔልን ጨምሮ ሶስት የባላስቲክ ሚሳዔሎች ማስወንጨፏን ደቡብ ኮሪያ አስታወቀች።
ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ጠዋት ላይ የባላስቲክ ሚሳዔሎቹ ወደ ምስራቅ ባህር ማስወንጨፏንም የደቡብ ኮሪያ ጦር ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
ሰሜን ኮሪያ መጀመሪያ ላይ ያስወነጨፈችው አህጉር አቋራጭ ባላስቲክ ሚሳዔል መሆኑ የተገመተ ሲሆን፤ 540 ኪሎ ሜትር ገደማ የተጓዘ መሆኑ የደቡብ ኮቲያ ጦር ጠቅላይ አዛዥ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።
ሁለተኛው ሚሳዔል ከመሬት በ20 ኪሎ ሜትር ከፍታ ላይ በመብረር ላይ እያለ ከእይታ መሰወሩን ያስታወቀችው ደቡብ ኮሪያ፤ 3ኛ ሚሳዔል ደግሞ በ60 ኪሎ ሜትር ከፍታ 760 ኪሎ ሜትሮችን ያክል መጓዙ ተነግሯል።
የጃፓን መከላከያ ሚኒስቴር በቶክዮ በሰጠው መግለጫ፤ ሰሜን ኮሪያ አዲስ ያሰወነጨፈቻቸው ሚሳዔሎች ያልተመለደ አይነት ፍጥነት እንደተስተዋለባቸው አስታውቋል።
ሰሜን ኮሪያ ሚሳኤሎች ከተወነጨፉ በኋላ አቅጣጫቸውን በመቀየር እንዲንቀሳቀሱ የሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎችን እየገነባች መሆኑ ተነግሯል።
ከእነዚህም ውስጥ “ሃይፐርሶኒክ ገሊድ ቴክኖሎጂ” አንዱ ሲሆን፤ ይህ ቴክኖሎጂ ሚሳዔሎችን በአየር መቃወሚያ ስርዓቶች ለመምታት አጋዳች ያደርገዋል ተብሏል።
ሰሜን ኮሪያ የፈረንጆቹ 2022 ከገባ ባለፉት 5 ወራ ውስጥ የዛሬ ጠዋቱን ጨምሮ 17 የባላስቲክ ሚሳዔል ሙከራዎችን ማድረጓ ተነግሯል።
ሀገሪቱ ካስወነጨፈቻቸው ሚሳዔሎች ውስጥ አውሬው የሚል መጠሪያ የተሰጠው አህጉር አቋራጭ የባላስቲክ ሚሳዔል ይገኝበታል።