ኪም “ጊዜው የውትድርና ንድፈ ሃሳብ፣ ልምምድና ትምህርት ክፍሎችን ማዘመንን ይጠይቃል" ብለዋል
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኮም ጆንግ ኡን ሀገራቸው የአጥፍቶ ጠፊ ድሮኖችን በስፋት እንደታመርት ትእዛዝ መስጠታቸው ተነግሯል።
ኪም ጆንግ ኡን በሰሜን ኮሪያ መመረት የጀመሩ የአጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች ሙከራ ላይ ታድመው የተመለከቱ ሲሆን፤ እንደዚህ አይነት ድሮኖች መምጣታቸው የወታደራዊ ንድፈ ሐሳቦች ላይ በአስቸኳይ ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ያመላክታል ብለዋል።
ኪም ከወራቶች በፊትም የአጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች ምርት እና ሙከራን ተመልከተው ነበር የተባለ ሲሆን፤ ሰሜን ኮሪያ የድሮኖቹን በፍጥነትና በስፋት ማምረት የጀመረችው ከሩሲያ ቴክኒካዊ ድጋፍ አንግኝታ ሳይሆን አይቀርም በሚል ስጋትም ፈጠሯል።
“ሎይትሪንግ ጥይቶች” በመባል የሚታወቁት እነዚህ አትፍቶ ጠፊ ድሮኖች በዩክሬን እንዲሁም በመካከለኛው ምስራቅ በጦርነት ውስጥ በስፋት ጥቅም ላይ መዋላቸው ይነገራል።
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኮም ጆንግ ኡን በድሮኖቹ ዙሪያ በሰጡት አስተያየት፤ በተቻለ ፍጥነት ዘላቂነት ያለው የምርት ስርዓት መገንባት እና ወደ ሙሉ የጅምላ ምርት መግባት እንደሚያስፈልግ አሳስቧል" ሲል የመንግስት የዜና ወኪል ኬ.ሲ.ኤን.ኤ ዘግቧል።
ኪም ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮኖችን) ለወታደራዊ አገልግሎት የመጠቀም ፉክክር በአለም ዙሪያ እየተፋጠነ መሆኑንም ገልጸዋል።
"እንዲህ ዓይነቱ ተጨባጭ ለውጥ ብዙ የውትድርና ንድፈ ሃሳብ፣ ልምምድ እና ትምህርት ክፍሎችን ማዘመንን ይጠይቃል" ብለዋል ኪም በንግግራቸው።
ከሚሳዔልና ኒኩሌር ጋር ተያይዞ ስሟ በስፋት የሚነሳው ሰሜን ኮሪያ ድሮኖችንም የምትጠቀም ሲሆን፤ ድሮኖቿ ድንበር በመጣስ ወደ ጎረቤት ደቡብ ኮሪያ በመግባት ውዥንብር መፍጠራቸውም ይታወሳል።
ሰሜን ኮሪያ ድንበር በመጣስ የላከቻቸው ድሮኖች በደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንታዊ ጽህፈት ቤት ዙሪያ እንዲሁም በረራ ክልክል የሆነባው ቁልፍ ቦታዎች ላይ ድሮኖቿን አብርራ እንደነበረም አይዘነጋም።
ይህም ደቡብ ኮሪያ የሰሜን ኮሪያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮኖችን) ለመምታት የጦር መሳሪያ እንድታሰማራ አስገድዷት ነበር።