የሰሜን ኮሪያው መሪ የአሜሪካን ጥቃት ለመቋቋም አዳዲስ ባሊስቲክ ሚሳይሎች እንዲመረቱ አዘዙ
ፕሬዝዳንቱ፤ሰሜን ኮሪያ የመጀመሪያውን ወታደራዊ የስለላ ሳተላይት ለማምጠቅ ጫፍ ላይ ደርሳለች ሲሉም ተናግረዋል
ኪም ጆንግ ኡን፤ አሁን ያለው ሁኔታ ወታደራዊ ጡንቻን ማሳደግ ሚጠይቅ ነው ብለዋል
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን በአሜሪካ የሚመራውን ስጋት ለመከላከል አዳዲስ አህጉር አቀፍ ባሊስቲክ ሚሳይሎችን እና ትልቅ የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎች እንዲመረቱ ጥሪ ማቅረባቸውን የመንግስት ሚዲያዎች ዘግቧል፡፡
ኪም ጆን ኡን በገዥው የሰራተኞች ፓርቲ ስብሰባ ላይ እንደተናገሩት ከሆነ ፤ የሀገራቸውን ሉዓላዊነት እና ደህንነት ለመጠበቅ "አስተማማኝ ወታደራዊ ኃይልን" ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
ስብሰባው ባለፈው ሳምንት የሰሜን ኮሪያ ድሮኖች ወደ ደቡብ በመግባታቸው ምክንያት በሁለቱም ኮሪያዎች መካካል የተፈጠረውን ውጥረት ተከትሎ የተደረገ ነው ተብሏል፡፡
የሰሜን ኮሪያ ድርጊት ያሳሰባቸው የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ-ዮል ከሰሜን ኮሪያ ሊቃጣ ለሚችለው ትንኮሳ አጸፋዊ ምላሽ ለመስጠት አስፈላጊውን ዝግጅት እንደደረገ ወታዳራዊ መኮንኖቻቸውን ማሳሳባቸው ከጽህፈት ቤታቸው የወጡ መግለጫዎች ጠቁመዋል።
ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ-ዮል ከወታደራዊ መኮንኖቻቸው ጋር በስልክ ሲደውሉ "ጠንካራ የአእምሮ ዝግጁነት እና የተግባር ስልጠና" እንደደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ኪም ጆንግ ኡን ዋሽንግተን እና ሴኡል ፤ አሜሪካ የኒውክሌር ጥቃት መሳሪያዎቸን በደቡብ ኮሪያ ውስጥ ያለማቋረጥ እያሰማራች ባለችበት ወቅት ፒዮንጊያንግን "ለመገለል እና ለማፈን" ሞክረዋል ሲሉ ይከሳሉ፡፡
የሀገራቱ ድርጊት “በሰው ልጅ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ” ሲሉም ኮንነውታል፡፡
ፒዮንጊያንግ አሜሪካ ከምትመራው ኃይል ሊሰነዘርባት የሚችለውን ጥቃት ለመመከት አቅዳ እየሰራቸው ነው ያሉት ኪም፤የሀገሪቱን የኒውክሌር ሃይል ለማጠናከር በተያዘው እቅድ መሰረት አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳይሎችን ለመስራት በመንቀሳቀስ ላይ መሆኗን አስታውቀዋል፡፡
“አሁን ያለው ሁኔታ ወታደራዊ ጡንቻን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ተደጋጋሚ ጥረቶችን ማድረግን ይጠይቃል” ሲሉም ተናግረዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡
አክለውም ደቡብ ኮሪያ “በማይታወቁ እና አደገኛ የጦር መሳሪያዎች ግንባታዎችን በመካሄድ” እና የጥላቻ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች በማድረግ “የእኛ የማያጠራጥር ጠላት ሆናለች” ብለዋል፡፡
ታክቲካል የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎችን በጅምላ የማምረት እና የሀገሪቱን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ በከፍተኛ ደረጃ እንዲጨምር ማድረግ የ2023 የኒውክሌር እና የመከላከያ ስትራቴጂ "ዋና አቅጣጫ" እንደሚሆንም ጭምር ፡፡
የሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት ኪም ጆን ኡን፤ ሀገሪቱ የስለላ ሳተላይት ለመስራት የምታደርገውን ጥረት በማፋጠን የመጀመሪያውን ወታደራዊ ሳተላይት ለማምጠቅ ጫፍ ላይ መሆኗም አስታውቀዋል፡፡