ኪም ጆንግ ኡን፤ ከእኛ ጋር ግጭት ውስጥ ለመግባት የሚፈልግን ማንኛውንም ሀገር "እናጠፋለን" ሲሉ ዛቱ
ኪም የኒውክሌር ኃይላቸውን " ሪፐብሊኩ የጣለባችሁን ኃላፊነት ለመፈጸም ዝግጁ መሆን አለባችሁ" ሲሉ አሳስቧል
የወቅቱ የሰሜን ኮሪያ ወታደራዊ እንቅስቀሴ ለደቡብ ኮሪያውያን ትልቅ ስጋት መሆኑ እየተገለጸ ነው
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን፤ ከእኛ ጋር ግጭት ውስጥ ለመግባት የሚፈልግን ማንኛውንም ሀገር "እናጠፋለን" ሲሉ ዛቱ፡፡
ኪም ጆንግ ኡን ይህን ያሉት የሰሜን ኮሪያ ጦር ሃይሎች ምስረታ ቀን፤ በተከበረበትና በከፍተኛ ወታዳራዊ ትርኢት በታጀበው በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ነው፡፡
ማንኛውም ሀገር ሰሜን ኮሪያ ከነካ አጸፋው የከፋ እንደሚሆን ያስጠነቀቁት ኪም ጆንግ ኡን፤ ፒዮንግያንግ አሁንም ቢሆን የኒውክሌር ጦር መሳሪያ እድገትን ለማፋጠን ጠንክራ ትሰራለችም ብለዋል፡፡
ኪም "በማንኛውም ጊዜ ሪፐብሊኩ የጣለባችሁን ኃላፊነት የተሞላበት ተልእኮ እና ልዩ መከላከልን ለመፈጸም ዝግጁ መሆን አለባችሁ" የሚል መልእክት ለኒውክሌር ኃይል ማስተላለፈቻውም የሰሜን ኮሪያ የዜና አገልግሎት ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡
የሰሜን ኮሪያ የኒውክሌር ሃይል ተቀዳሚ ተልእኮ ጦርነትን ማስቆም ቢሆንም፤ ሌሎች ሀገራት የማይፈለጉ ጫናዋች የሚፈጥሩ ከሆነ ግን ተልእኮው ይህ ብቻ ላይሆን ይችላል ሲሉም አክሏል።
ኤጀንሲው እንዳስታወቀው፤ የተካሄደው የወታደራዊ ሰልፍ ትርኢቱ የሰሜን ኮሪያ ትልቁ አህጉር አቋራጭ ባለስቲክ ሚሳኤል ኤችዋሶን-17 ያካተተ ነው።
ለመጀመሪያ ጊዜ ባለፈው ወር የተሞከረው ግዙፉ ሚሳኤል ፤ በደቡብ ኮሪያ በኩል ትልቅ ቁጣ መቀስቀሱ የሚታወስ ነው፡፡
ደቡብ ኮሪያ ፤ “ኪም ሚሳኤሉን ለመሞከር ሙሉ ጥረት ቢያደረጉ ፒዮንግያንግ ላይ ሌላ መዘዝ ይዞ እንደሚመጣ ሊያውቁ ይገባል” ስትል በወቅቱ ማስጠንቀቋ አይዘነጋም፡፡
ፒዮንግያንግ የኒውክሌርን ማበልጸግ እቅዶቿን ለመሰረዝ ከአሜሪካ ጋር ድርድር በጀመረችበት የተካሄደው ይህ አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤሎችንና መድፍ እና ታንኮች ያሉ የተለመዱ መሳሪያዎችን ሳይቀር ለእይታ የቀረቡበት ወታደራዊ ሰልፉ በበርካቶች ዘንድ ጥያቄ መፍጠሩ አልቀረም፡፡
ሰልፉ ለኪም ጆንግ ኡን "ረዥም ህይወት" የሚመኙ መዝሙሮች የተደመጡበትም ነበር፡፡