ከአሜሪካ ስጋት ተደቅኖብናል ያሉት ኪም የሚሳይል ጦር ሰፈሮችን ጎበኙ
ኪም በጦር ሰፈሮቹ ጉብኝት ያደረጉት ከሴኡል እና አጋሮቿ ጋር ያለው ውጥረት በተካረረበት ወቅት ነው
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የሚሳይል ጣቢያዎችን ጥቃት የመከላከል ዝግጁነት ለመፈተሽ ጉብኝት ማድረጋቸው ተገልጿል
ከአሜሪካ ስጋት ተደቅኖብናል ያሉት ኪም የሚሳይል ጦር ሰፈሮችን ጎበኙ መጎብኘታቸው ተገልጿል።
የአሜሪካ የኑክሌር ጦር መሳሪያ አቅም ለሀገሪቱ ስጋት መሆኑን የጠቀሱት የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን የሚሳይል ጣቢያዎችን ጥቃት የመከላከል ዝግጁነት ለመፈተሽ ጉብኝት ማድረጋቸውን ቢኦቬ ኬሲኤንኤን ጠብሶ ዘግቧል።
እንደዘገባው ከሆነ ኪም የአሜሪካ ስትራቴጂክ ኑክሌር ጦር መሳሪያ ለሰሜን ኮሪያ ከፍተኛ ስጋት መደቀኑ ፒዮንግያንግ የኑክሌር ኃይሏን ዝግጁ እንድታደርግ ያስገድዳታል ብለዋል።
የባለስቲክ ሚሳይል እና የኑክሌር ጦር መሳሪያ ልማቷን እያጠናከረች ያለችው ሰሜን ኮሪያ ከሩሲያ ጋርም ወታደራዊ ግንኙነት ጀምራለች። ይህ የሰሜን ኮሪያ ተግባር አለምአቀፍ ማዕቀቦችን አስከትሎባታል።
ኪም በጦር ሰፈሮቹ ጉብኝት ያደረጉት ከሴኡል እና አጋሮቿ ጋር ያለው ውጥረት በተካረረበት ወቅት ነው።
ውጥረቱን ካባባሱት መካከል ሴኡል፣ ሰሜን ኮሪያ ወታደሮቿ በዩክሬን ጦርነት ከሩሲያ ጎን ሆነው እንዲዋጉ ልካለች የሚል ክስ ማቅረቧ ይገኝበታል።
ሰሜን ኮሪያ ግን ወደታሮች ወደ ዩክሬን ልካለች የሚለውን ክስ አስተባብላለች።
የደቡብ ኮሪያ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሺን ዋን ሲክ እና የፖላንድ ብሔራዊ ደህንነት ቢሮ ኃላፊ ጃሴክ ሲውይራ ፒዮንግያንግ ከሞስኮ ጋር ያላት ወታደራዊ ትብብር እንደሚያሰጋቸው ሴኡል በነበረው ስብሰባ ተናግረዋል።
ከደቡብ ኮሪያ ፕሬዝደንት ጽ/ቤት እንደወጣው መግለጫ ከሆነ ሁለቱ በጉዳዩ ላይ ከአለምአቀፉ ማህበረሰብ ጋር ለመተባበር ተስማምተዋል።
ኬሲኤንኤ እንዳለው ከሆነ ኪም የሀገሪቱ ጦር ለስትራቴጂክ የሚሳይል ትኩረት በመስጠት እንዲዘምን ጥሪ አቅርበዋል።
በቅርቡ ኪም የአሜሪካ ዋነኛ አጋር የሆነችውን ደቡብ ኮሪያን "ጠላት ሀገር" ሲሉ መፈረጃቸው ይታወሳል።