በወርቅና በውድ ግብዓቶች የሚሰራው የሳዑዲው ከዓባ ሽፋን (ኪስዋ) የመቀየር ስነ ስርዓት ተካሄደ
የአንዱ የከዓባ ልብስ ዋጋም 17 ሚሊየን የሳዑዲ ሪያል አሊያም 4.53 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ያወጣል
ኪስዋ የከዓባ ልብስ 1 ሺህ ኪሎ ግራም ጥቁር ሲልክ፣ 120 ኪሎ ግም ወርቅና 100 ኪሎ ግራም በብር ገመድ ነው የሚዘጋጀው
የሳዑዲ አረቢያ የሁለቱ ቅዱስ መስጊዶች አስተዳደር የጥገና እና የንብረት አስተዳደር ክፍል የከዓባ ግንብ ሽሃን ልብስ (ኪስዋ) የመቀየር ስነ ስርዓት እየተካሄደ መሆኑን አስታውቋል።
የከዓባ ሽፋን (ኪስዋ) የመቀየር ስነስርዓት በየዓመቱ የሚከናወን ሲሆን፤ ዘንድሮም የሂጅራ ዘመን አቆጣጠር በአዲስ ዓመት መጀመሩን ተከትሎ ነው የተከናወነው።
በዚህም ከቁርዓን የተወሰዱ ጥቅሶች ያሉበት እና ከውድ ግብዓቶች የተዘጋጀው የከዓባው ልብስ (ኪስዋ) እንዲወርድ በማድረግ በአዲሱ ልብስ የመቀየር ስራ ተካሂዷል ነው የተባለው።
ኪስዋ በተባለ ኢንደስትሪ የሚዘጋጀው የከዓባው ልብስ 1000 ኪሎ ግራም ጥቁር ሲልክ፣ 120 ኪሎ ግም ወርቅ እና 100 ኪሎ ግራም በብር ገመድ ነው የሚዘጋጀው።
የአንዱ የከዓባ ልብስ ዋጋም 17 ሚሊየን የሳዑዲ ሪያል አሊያም ከ4.5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ እንደሚያወጣም ነው የተነገረው።
አሮጌው ኪስዋ በትናንሽ ቁርጥራጮች ተቆርጦ ለእስልምና እምነት ተከታዮች የሚሰጥ መሆኑም ተነግሯል።