ሞሃመድ ሳላህ የሊቨርፑል የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አግቢ ሆነ
ሳላህ በ5 ተከታታይ ጨዋታዎች በማንቸስተር ዩናትድ ላይ ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያው የሊቨርፑል ተጨዋች ሆኗል
በ26ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሊቨርፑል ማንቸስተር ዩናይትድን 7ለ0 ማሸነፉ ይታወቃል
ግብጻዊው የፊት መስመር ሞሃመድ ሳላህ የሊቨርፑል የምንግዜም ከፍተኛ ግብ አግቢ ሆነ።
ሳላህ የክለቡ ከፍተኛ ግብ አስቀጣሪ መሆን የቻለው ሊቨርፑል ማንቸስትር ዩናይትድን 7 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ባሸነፈበት በትናንቱ ጨዋታ ላይ ሁለት ጎሎችን ማስቆጠሩን ተከትሎ ነው።
በዚህም የ30 አመቱ ሳለህ እስካሁን 129 ግቦችን በማስቆጠር ቀደም ሲል በክለቡ አንጋፋ ተጨዋች ሮቢ ፉለርን (128 ግቦች) ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን መስበር ችሏል።
ሊቨርፑልን ከማንችሰተር ዩናትድ ባገናኘው የትናት ምሽት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ሊቨርፑል ማንቸስተር ዩናይትድን 7ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።
በጨዋታውም የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ጎሎች ጋብኮ፣ ኑኔዝ እና ሳላህ እያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ግቦችን ከመረብ ሲያሳርፉ፤ ፈርሚኒሆ 7ኛውን ጎል ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።
የትናት ምሽቱን ጨዋታ ተከትሎ ሞሃመድ ሳላህ በ5 ተከታታይ ጨዋታዎች በማንቸስተር ዩናትድ ላይ ግብ ያስቆጠረ የመጀመሪያው የሊቨርፑል ተጨዋች ሆኗል።
ስቴቨን ጄራርድ (120 ግቦች) እና ማይክል ኦወን (118 ግቦች) በክለቡ ታሪክ ከፍትኛ ግብን በማስቆጠር ሶስተኛ እና አራተኛ ደረጃ ላይ የሚቀቀመጡ ናቸው።
ሳላህ በውድድር ዘመኑ በሊጉ ያስቆጠራቸው ግቦችም ወደ 11 ከፍ አድርጓል።
ግብጻዊው ኮከብ ከሮማ ወደ ሊቨርፑል በመጣበት በ2017/18 የውድድር ዘመን በነበሩት ወርቃማ ጊዜያት 32 ግቦችን በማስቆጠር የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ እንደነበር አይዘነጋም፡፡