ፖለቲካ
የኩዌት ኤሚር ናዋፍ አል-አሕመድ አል-ሳባህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
ሼክ ናዋፍ አል-አሕመድ አል-ሳባህ ባጋጠማቸው የጤና ችግር በ86 ዓመታቸው አርፈፈዋል
ኤሚር ናዋፍ አል-አሕመድ አል-ሳባህ በፈረንጆቹ 2020 ነበር ኩዌትን መምራት የጀመሩት
የኩዌት ኤሚር ሼክ ናዋፍ አል-አሕመድ አል-ሳባህ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።
በህዳር ወር መጀመሪያ አካባ ያጋጠማቸውን ጤና ቸግር ተከትሎ ወደ ሆስፒታል የገቡት ሼክ ናዋፍ አል-አሕመድ አል-ሳባህ በ86 ዓመታቸው አርፈፈዋል።
ሼክ ናዋፍ አል-አሕመድ አል-ሳባህ ከሦስት ዓመት በፊት በፈረንጆቹ 2020 በሥልጣን ላይ የነበሩትን የወንድማቸውን ሕልፈት ተከትሎ ነበር ወደመሪነት የመጡት።
የሀገሪቱ የመንግስት በቴሌቪዥን ዛሬ ባሰራጨው መግለጫ፤ “በታላቅ ሀዘን ሼክ ናዋፍ አል-አሕመድ አል-ሳባህ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን እናሳውቃለን” ብሏል።
በፈረንጆቹ በ1937 የተወለዱት ሼክ ናዋፍ አል-አሕመድ አል-ሳባህ የኩዌት የቀድሞ ገዥ ሼክ አህመድ አል-ጀብር አል ሳባህ አምስተኛ ልጅ ነበሩ።
ሼክ ናዋፍ አል-አሕመድ አል-ሳባህ በፈረንጆቹ በ2006 የልኡል አልጋ ወራሽነትን ስፍራ የያዙ ሲሆን፤ በፈረንጆቹ 2020 ደግሞ የኩዌት ኤሚር በመሆን ተሹመዋል።
ሼክ ናዋፍ አል-አሕመድ አል-ሳባህ ህልፈትን ተከትሎ ልኡል አልጋ ወራሽ የነበሩት የ83 ዓመቱ ሼክ ማሻል አል አህመድ አል ሳባህ የኩዌት ኤሚርነት ስፍራን ተረክበዋል።