ኪሊያን ምባፔ “ህልሜ እውን ሆኗል፤ የልጅነት ምኞቴ የነበረውን ክለብ በመቀላቀሌ ደስታና ኩራት ይሰማኛል” አለ
ኪሊያ ምባፔ የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድን በይፋ ተቀላቅሏል

ኪሊያን ምባፔ በሪያል ማድሪድ ቤት 9 ቁጥር ማልያ እንደሚለብስ ይጠበቃል
ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ሪያል ማደሪድን መቀላቀሉን ተከትሎ “ህልሜ እውን ሆኗል፤ የልጅነት ምኞቴ የነበረውን ክለብ በመቀላቀሌ ደስታና ኩራት ይሰማኛል” ብሏል።
የስፔኑ የእግር ኳስ ክለብ ሪያል ማድሪድ ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ ከፈረንሳዩ ፒኤስጂ በነፃ ዝውውር ማስፈረሙንትናንት ምሽት ይፋ አድርጓል።
ኪሊያን ምባፔ ለሪያል ማድሪድ እስከ 2029 የውድድር ዘመን የሚያቆየውን የአምስት አመት ኮንትራት መፈረሙም በትናትናው እለት ይፋ ተደርጓል።
ኪሊያን ምባፔ ለሪያል ማድሪድ በመፈረሙ ምክንያት የፊርማ ጉርሻ በአምስት አመታት ተከፋፍሎ የሚከፈል 100 ሚልዮን ዩሮ እንደሚያገኝ ተገልጿል።
ኪሊያን ምባፔ በሪያል ማድሪድ ቤት ቆይታው በቀጣዩ 2024/25 የውድድር ዘመን 9 ቁጥር ማልያ እንደሚለብስ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህ የሆነውም ኪሊያን ምባፔ እና ሪያል ማድሪድ አሁን ላይ 10 ቁጥር ለብሶ ለሚጫወተው ሉካ ሞድሪች ካላቸው ክብር የተነሳ ነው ተብሏል።
ኪሊያን ምባፔም ይሁን ወኪሎቹ በቀጣዩ የውድድር ዘመን ላይ 10 ቁጥር ማሊያን ለመልበስ ጥያቄ እንዳላቀረቡም ምንጮች ተናግረዋል።
በዚህም መሰረት በቀጣዩ 2024/25 የውድድር ዘመን ሉካ ሞድሪቸች 10 ቁጥር ማሊያ ኪሊያን ምባፔ ድገሞ 9 ቁጥር ማሊያ ለብሰው እንደሚጫወቱም ነው የተነገረው።
ኪሊያን ምባፔ 10 ቁጥር ማያን ለመልበስ ልክ ክርስቲያኖ ሮናልዶ 7 ቁጥርን ለመልበስ ራውልን እንደጠበቀው ሉካ ሞድሪችን ይጠብቃል ተብሏ።
ፈረንሳዊውን የፊት መስመር ተጨዋች ኪሊያን ምባፔ 10 ቁጥር ማያን በቀጣይዓመት ከሰኔ ወር በኋል ከሉካ ሞድሪችን እንደሚረከብ ተዘግቧል።
ኪሊያን ምባፔ የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድን በይፋ መቀላቀሉን ተከትሎም በማበራዊ ሚዲያ ገጾቹ ላይ በልጀነቱ የክለቡ ማሊያን ለብሶ እንዲሁም ከተጫዋቾቹ ጋር የተነሳቸውን ፎቶዎች በማጋራት ደስታውን ገልጿል።
ምባፔ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባጋራው ጽሁፍም "ህልሜ እውን ሆነ፤ሁሌም ወደማልመው ክለቤ ሪያል ማድሪድ በመቀላቀሌ ደስታ እና ኩራት ይሰማኛል” ብሏል።
“አሁን ምን ያህል ደስተኛ እንደሆንኩ ማንም ሊረዳ አይችልም” ያለው ምባፔ፤ ማድሪዲዳውያን ሲል የጠራውን የክለቡን ደጋፊዎችም “እናንተን ለማየት ጓጉቻለሁ፤ ላደረጋችሁልኝ ድጋፍም አመሰግናለሁ" ሲል አስፍሯል።