ምባፔ ከፒኤስጂ ሊለቅ መሆኑን ተናገረ
ፒኤስጂ አምስት የሊግ ዋን ድሎችን እንዲያገኝ ያደረገው የ25 አመቱ አጥቂ በ290 ጨዋታዎች ተሰልፎ 243 ግቦችን አስቆጥሯል።
የፈረንሳዩ አምበል ክሊያን ምባፔ ከፓሪስ ሴንት ጄርሜን እንደሚለቅ ለክለቡ አሳወቀ
ምባፔ ከፒኤስጂ ሊለቅ መሆኑን ተናገረ።
የፈረንሳዩ አምበል ክሊያን ምባፔ ከፓሪስ ሴንት ጄርሜን(ፒኤስጂ) እንደሚለቅ ለክለቡ ማሳወቁን ሮይተርስ ዘ አትሌቲክስ ዌብሳይትን ጠቅሶ ዘግቧል።
ምባፔ በፒኤስጂ ለሰባት አመታት ያህል ተጫውቷል።
የ2018ቱ የአለም ዋንጫ ሁለተኛ ሆኖ ያጠናቀቀው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አባል የነበረው ምባፔ በ222 ሚሊዮን ዩሮ ከተቀላቀለው ብራዚላዊዉ ኔይማር ቀጥሎ በ94 ሚሊዮን ዶላር ሁለተኛ ውድ ተከፋይ ሆኖ ነበር በ2017 ከሞናኮ ወደ ፒኤስጂ የተቀላቀለው።
"ምባፔ ውሳኔውን ለክለቡ አሳውቋል፤ ነገር ግን በሚወጣበት ሁኔታ ላይ ከስምምነት ላይ አልተደረሰም። ሁኔታዎቹ ሲጠናቀቁ በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ ይፋ ይደረጋል" ብሏል ዘገባው።
ፒኤስጂ አምስት የሊግ ዋን ድሎችን እንዲያገኝ ያደረገው የ25 አመቱ አጥቂ በ290 ጨዋታዎች ተሰልፎ 243 ግቦችን አስቆጥሯል። ምባፔ የክለቡ የምንግዜም ግብ አስቆጣሪ በመሆን እየመራ ነው።
ክለቡ እስካሁን በጉዳዩ ላይ አስተያየት አለመስጠቱን ዘገባው ጠቅሷል።
ምባፔ ባለፈው አመት ኮንትራቱ በመጭው ሰኔ ሲያልቅ ኮንትራቱን በአንድ አመት ማራዘም እንደማይፈልግ ለፒኤስጂ በደብዳቤ አሳውቆ ነበር።
ምባፔን በ200 ሚሊዮን ዩሮ ለማስፈረም ጠይቆ ነበር ከተባለው ሪያልማድሪድ ጋር ስሙ ሲነሳ ቆይቷል። በ2022ም በፒኤስጂ ያለው ኮንትራት በአንድ አመት ማራዘሙን ከማሳወቁ በፊት ወደ ላሊጋ ለመሄድ ፍላጎት አሳይቶ እንደነበር ይታወሳል።