ፖለቲካ
በሎስ አንጀለስ የሰደድ እሳት 30 ሺህ ሰዎች ከቤታቸው መፈናቀላቸው ተገለጸ
በከባድ ነፋስ የታጀበው የሰደድ እሳቱ ወደ 2 ሺህ 900 ሄክታር መሬት መስፋፋቱ ተገልጿል
በርካታ ሰዎች በእጅና ፊታቸው ላይ የቃጠሎ አደጋ መድረሱን የእሳት አደጋ ባለስልጣናት አስታውቀዋል
በአሜሪካዋ ሎስ አንጀለስ በተቀሰቀሰ የሰደድ እሳት 30 ሺህ ሰዎች ከቤታቸው መፈናቀላቸው ተገለጸ።
በሎስ አንጀለስ በትናትናው እለት ማክሰኞ የተቀሰቀሰው የሰደድ እሳቱ በስፍራው ባለው ነፋስ ሳቢያ በፍጥነት እየተዛመተ ነው የተበለ ሲሆን፤ በርታ ህንጻዎች በእሳቱ መውደማቸውም ተነግሯል።
የሰደድ እሳቱን ተከትሎ ከ30 ሺህ ሰዎች በላይ ከቤታው ተፈናቅለዋል የተባለ ሲሆን፤ እሳቱን በሚሸሹ ሰዎች ሳቢያ ከፍኛ የትራፊክ መጨናቅ መፈጠሩም ተሰምቷል።
በሰደድ እሳቱ እስካሁን ሳንታ ሞኒካ እና ማሊቡ በተባሉ አነስተኛ ከተሞች መካከል የሚገኝ ወደ 2 ሺህ 900 ሄክታር መሬት ላይ ቃጠሎ ማድረሱ ታውቋል።
የእሳት አደጋ መከላከል ባለሙያዎች በእሳት አደጋው በርካታ ሰዎች በእጅና ፊታቸው ላይ የቃጠሎ አደጋ መድረሱን ተናግረዋል።
በደቡብ ካሊፎርኒያ ሎስ አንጀለስ የተከሰተው ሰደድ እሳት ከፍተኛ ነፋስ የቀላቀለ በመሆኑ አሁን ላይ በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ነው ተብሏል፡፡
አደጋውን ተከትሎም በከተማዋ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን÷ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የተጎዱ አካባቢዎችን ለመደገፍ የሚውል በጀት እድቀዋል።