በወላይታ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አደጋው ዛሬ ረፋድ በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ ነው የደረሰው
በመሬት መንሸራተት አደጋው የሞቱ ሰዎች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ተነግሯል
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ በመሬት መንሸራተት አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ።
አደጋው ዛሬ ረፋድ 5 ሰዓት አካባቢ መድረሱን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ኮሚዩኒኬሽን ያኘነው መረጃ ያመለክታል።
በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋው እስከ አሁን የ11 ሰዎች አስክሬን መገኘቱንም ወረዳው አስታውቋል።
በመሬት መንሸራተት አደጋው ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል የካዎ ኮይሻ ወረዳ አስተዳደሪ ሕዝቅኤል ጎቶሮ ተናግረዋል፡፡
ከቀናት በፊት በዚሁ አካባቢ በተከሰተ የመሬት ናዳ 1 ሰው ህይወቱ ማለፉ እና 1 ሰው ከባድ ጉዳት እንደረሰበት ይታወሳል።
ከሳምንት በፊት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ250 በላይ ሰዎች ህይወት ማለፉ ይተወሳል።
የገዜ ጎፋ የመሬት መንሸራተት አደጋን ተከትሎም በኢትዮጵያ የ3 ቀናት ብሄራዊ ሀዘን ተውጆ እንደነበረ ይታወሳል።