ከሬሚታንስ ከፍተኛ ገቢ በማግኘት ህንድ፣ ሜክሲኮና ቻይና ቀዳሚዎቹ ናቸው
በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ሰዎች ወደ ሀገራቸው የሚልኩት የውጭ ምንዛሬ (ሬሚታንስ) በ2023 የ3 ነጥብ 8 በመቶ እድገት አስመዝግቧል።
ባለፈው የፈረንጆቹ አመት በሬሚታንስ የተላከው ገንዘብ 669 ቢሊየን ዶላር መድረሱንም የአለም ባንክ መረጃ ያሳያል።
ህንዳውያን ከያሉበት ሀገር ለቤተሰብ ጓደኞቻቸው ከፍተኛ መጠን ያለው የውጭ ምንዛሬ (ሬሚታንስ) በመላክ ቀዳሚ ናቸው።
በሬሚታንስ ገቢ ከፈረንጆቹ 2008 ጀምሮ ቀዳሚ የሆነችው ህንድ በ2023 125 ቢሊየን ዶላር አግኝታለች።
ታጂኪስታን፣ ቶንጋ፣ ሊባኖስ እና ኒካራጋዋ ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርታቸው (ጂዲፒ) የሬሚታንስ ገቢያቸው ድርሻ ከፍተኛ የሆነባቸው ሀገራት ናቸው።
ሬሚታንስ በሀገራት ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ያለው ፋይዳ ቀላል የሚባል ባለመሆኑ ሀገራት ዜጎቻቸው የውጭ ምንዛሬ እንዲልኩ የሚያበረታቱ ጥቅማ ጥቅሞችን ያቀርባሉ።
ከሬሚታንስ ከፍተኛ ገቢ ያገኙ ሀገራትን በዝርዝር ይመልከቱ፦