ስፖርት
በኦሎምፒክ ታሪክ ዘጠኝ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነችው ላሪሳ ላቲኒና ማን ነች?
አትሌት ላሪሳ በኦሎምፒክ ውድድሮች ታሪክ 18 ሜዳሊያዎችን አግኝታለች
የጅምናስቲክ ስፖርተኛዋ ላሪሳ በሶስት የኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ መሳተፍ ችላለች
በኦሎምፒክ ታሪክ ዘጠኝ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት የሆነችው ላሪሳ ላቲኒና ማን ነች?
ላሪሳ ላቲኒና በቀድሞ የሶቭየት ህብረት በአሁኗ ዩክሬን ኬርሰን ግዛት በ1934 ኑበር የተወለደችው።
በሜልቦርን፣ ሮም እና ቶኪዮ ኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ ሶቪየት ህብረትን ወክላ ተወዳድራለች።
አትሌቷ በሶስቱ የኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ 18 ሜዳሊያዎችን ያሸነፈች ሲሆን ከዚህ ውስጥ ዘጠኙ ወርቅ፣ አምስት ብር እና አራት ነሀስ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።
አባቷ በልጅነቷ ከእናቷ ጋር መለያየቱን ተከትሎ በእናቷ ልፋት ብቻ ያደገችው አትሌት ላሪሳ በኦሎምፒክ ውድድሮች ስኬታማ ከሆኑ አትሌቶች መካከል ዋነኛዋ ነች።
የጅምናስቲክ ስፖርተኛዋ አትሌት ላሪሳ በሜልቦርን ኦሎምፒክ አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ስታመጣ በሮም ሶስት እንዲሁም በቶኪዮ ኦሎምፒክ ደግሞ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን አሸንፋለች።
አትሌቷ ለ48 ዓመታት በታሪክ ብዙ ሜዳሊያዎችን በማሸነፍ ክብረወሰን ይዛ ቆይታለች።
የአትሌቷ ብዙ ሜዳሊያዎችን የማሸነፍ ሪከርድ በ2012 በለንደን ኦሎምፒክ ውድድር ላይ በዋናተኛው ሚካኤል ፌልፕስ ተሰብሯል።