ስፖርት
ከ128 ዓመት በፊት በተጀመረው ኦሎምፒክ ውድድር ብዙ ሜዳሊያ ያገኘው ሀገር የትኛው ነው?
ፓሪስ ከ100 ዓመት በኋላ የዘንድሮውን ውድድር ልታዘጋጅ ሶስት ቀናት ብቻ ቀርተዋል
በውድድሩ ላይ ከ206 ሀገራት የተውጣጡ ከ10 ሺህ 500 በላይ አትሌቶች ይሳተፋሉ
ከ128 ዓመት በፊት በተጀመረው ኦሎምፒክ ውድድር ብዙ ሜዳሊያ ያገኘው ሀገር የትኛው ነው?
ተወዳጁ የኦሎምፒክ ውድድር በፈረንጆቹ 1896 ላይ በግሪክ የተጀመረ ሲሆን የዘንድሮው ውድድር በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።
ውድድሩ የፊታችን አርብ በይፋ የሚከፈት ሲሆን ከ206 ሀገራት የተውጣጡ ከ10 ሺህ 500 በላይ አትሌቶች እንደሚወዳደሩ ዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ አስታውቋል።
እስካሁን በተካሄዱት የኦሎምፒክ ውድድሮች ላይ አሜሪካ 2 ሺህ 629 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ በታሪክ ስኬታማዋ ሀገር ነች።
ከአሜሪካ በመቀጠል ሶቭየት ህብረት፣ ጀርመን እና ብሪታንያ ብዙ ሜዳሊያዎችን ካገኙ ሀገራት መካከል ተጠቅሰዋል።
ከአፍሪካ ኬንያ በ113 ሜዳሊያዎች በአንደኝነት ስትቀመጥ ደቡብ አፍሪካ በ89 እንዲሁም ኢትዮጵያ ደግሞ በ58 ሜዳሊያዎች በሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።