በርካታ ተከታታይ ያላቸው ተወዳጅ የስፖርት ውድድሮች
በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳጅ ከሆኑ የስፖርት ውድድሮች መካከል 3.5 ቢሊየን ህዝብ ተከታታዮች አሉት የተባለው እግር ኳስ ቀዳሚ ሆኗል
የስፖርት ውድድሮቹ ካላቸው ተመልካች ባለፈ ለመዝናኛነት የሚያዘወትሯቸው ሰዎች ቁጥርም ከፍተኛ ነው
ስፖርታዊ ውድድሮች በመዝናኛው አለም ከፍተኛ ተቀባይነት በርካታ ተመልካች እና ተወዳጅነት ካለቸው ዘርፎች መካከል ይጠቀሳሉ።
ውድድሮቹ ካላቸው ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተመልካች ባለፈ የሚያንቀሳቅሱት ኢኮኖሚም ግዙፍ ነው።
ስፖርት ብሪፍ የተባለው ድረገጽ በርካታ ተከታታይ ያላቸው ተወዳጅ የስፖርት አይነቶች በሚል ባወጣው ሪፖርት የስፖርት ውድድሮቹ እንደየአካባቢው ያላቸው ተቀባይነት እንደሚለያይ አስቀምጧል።
ስፖርቶቹ በተለያየ ዘርፍ የሚያድርጓቸው ውድድሮች የተመልካቾችን ቀልብ የሳበ ተወዳጅነታቸውም እንዲጨምር ያስቻለ ነው።
ለአብነት እግር ኳስ አለም አቀፋዊ ተወዳጅነት እንዲያገኝ የአለም ዋንጫ፣ የአህጉር ውድድሮች፣ የእንግሊዝ እና የስፔን ሊጎች ትልቁን ድርሻ ይወስዳሉ ።
እግርኳስ በአውሮፓ ፣ አፍሪካ እስያ እና በአሜሪካ ተወዳጅ የስፖርት አይነት ሲሆን በነዚህ ቀጠናዎች ስፖርቱን ከመመልከት ባለፈ በመዝናኛነት የሚያዘወትሩት ሰዎችም ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ ተጠቅሷል።
ድረ ገጹ እግርኳስ 3.5 ቢሊየን ወዳጆችን በመያዝ በአለም አቀፍ ደረጃ ባለው ተቀባይነት ቀዳሚው ነው ያለ ሲሆን ፤ በእስያ በአውስትራሊያ እና ብሪታንያ ተወዳጅ የሆነው የክሪኬት ስፖርት 2.5 ቢሊየን ተመልክች አልያም ተከታታዮችን በመያዝ ሁለተኛ እንደሆነ አስታውቋል።