ፖለቲካ
ብሪክስ የምዕራባውያን የበላይነት የማስቀጠል ሙከራ እንዲያበቃ አልሟል- ሴርጌ ላቭሮቭ
ወጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የምዕራባውያን የበላይነታቸውን የማስቀጠል የሚያደርጉት ሙከራ ተቃራኒውን ያስከትላል ብለዋል
ላቭሮቭ "ዛሬ በዓለም አስደንጋጭ የሚባሉ ለውጦች እየተካሄደ ነው። ብዝሃነት ያለው የዓለም ስርአት ብቅ ሲል እያየን ነው" ብለዋል
የእስያዎቹ ኋያላን ሩሲያ እና ቻይና ያሉበት ብሪክስ የተባለው ጥምረት አላማው ፍትህ እንደሆነ እና ብዝሃነት ያለው የዓለም ስርአት እንዲፈጠር መስራት መሆኑን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒክቴር ስርጌ ላቭሮቭ ተናገረዋል።
ወጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የምዕራባውያን የበላይነታቸውን የማስቀጠል የሚያደርጉት ሙከራ ተቃራኒውን ያስከትላል ብለዋል።
በምዕራባውያን የበላይነት የሚመራው የአለም ስርአት የሀብት ምዝቀራ ሞዴል ስለሆነ አዛኛው አለም ሊያጠፋው ይገባል ሲሉም ተናገረዋል።
ላቭሮቭ "ዛሬ በዓለም አስደንጋጭ የሚባሉ ለውጦች እየተካሄደ ነው። ብዝሃነት ያለው የዓለም ስርአት ብቅ ሲል እያየን ነው" ብለዋል
ብሪክስ ለመሰል ሀገራት ብዝሃነት ያለው የዓለም ስርአት ምሳሌ ነው ያሉት ላቭሮቭ ጥምረት በዓለም ደቡባዊ ክፍል ምስራቅ ያሉ ሀገራት ትብብር ያጠናክራል ብለዋል።
የምዕራባውያን የበላይነትን ለመገዳደር የተቋቋመው ብሪክስ፣ አዲስ የመገበበያ ገንዘብ ይፋ ለማድረግ እና ዶላር ከገበያ ውጭ እንዲሆን እየሰራ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል።