የዳርፉር አማጺ መሪ የሱዳን የፋይናንስ ሚኒስትር ሆነው በጠ/ሚ ሀምዶክ ተሾሙ
አዲሱ የካቢኔ ሹመት የተደረገው በፈረንጆቹ ጥቅምት ወር መንግስት ከአንዳንድ አማጺዎች ጋር ያደረገውን ስምምነት መሰረት አድርጎ ነው
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሹመት ለቀድሞው የአልበሽር ተቃዋሚ ኡማ ፓርቲ መሪ ልጅ መሪየም ሳዲቅ አልማሃዲ ተሰጥቷል
የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ የመንግስታቸውን ካቢኔ በድጋሚ ሲያዋቅሩ የዳርፉር አማጺ መሪ ጅብሪል ኢብራሂምን የፋይናንስ ሚኒስትር አድርገው ሾመዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ ካቢኔ ያዋቀሩት የጀመሩትን ሪፎርም ከማስቀጠልና በሀገሪቱ ያለውን የኢከኖሚ ቀውስ ለመፍታትና የውጭ የፋይናንስ ለማምጣት በሚታገሉበት ወቅት ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀምዶክ የተሾሙት ሱዳንን 30 አመታት ለሚጠጋ ጊዜ የመሩት ኦመር አልበሸር በመፈንቅለ መንግስት ከተወገዱ በኋላ ነበር፡፡
ከፈረንጆቹ ሀምሌ ጀምሮ የፋይናንስ ሚኒስትር ጨምሮ ሰባት ሚኒስቴሮች በባለአደራ ሚኒስትሮች ሲመሩ ቆይተዋል፡፡ አዲሱ የካቢኔ ሹመት የተደረገው መንግስት በፈረንጆቹ ጥቅምት ወር ከአንዳንድ አማጺዎች ጋር በተደረገው የሰላም ስምምነት ነው፤የስምምነቱ አላማም በዳርፉርና በደቡባዊ ሱዳን ግጭቶችን ለማስቆም ነበር፡፡
የጀስቲስ ኤንድ ኢኳሊቲ ሞቭመንት(ጄኢኤም)መሪ የሆነው ኢብራሂም በዳርፉር ከመንግስትን ጦር ጋር ከፈረንጆቹ 2003 ጀምሮ ሲዋጉ የነበረ ሲሆን ቀደም ሲልም በአልበሽር ስር የነበረው የእስላማዊ እንቅስቃሴ አባል ነበሩ፡፡ የቀድሞው የጄኢኤም የኢኮኖሚ አማካሪ የነበሩትና የቀድሞውን የአልበደሽር አጋር ኢብራሂም ሀገሪቱ በኢኮኖሚ ቀውስ ውስጥ ባለችበት ጊዜ መሾም፤ እንደአንዳንድ ሱዳናውያንና ተንታኖች ጥያቄ ውስጥ አስገብተውታል፡፡
ሌሎች አማጺያንም የማእድን፣የላይቭስቶክ፤የማህራዊ ልማት፤የትምህርትና የፌደራል ሚኒስትሪዎችን እንዲመሩ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት ሶስት የአማጺ መሪዎች የሽግግር ምክርቤቱ አባል እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሹመት ለቀድሞው የአልበሽር ተቃዋሚ ኡማ ፓርቲ መሪ ሳዲቅ አልማሃዲ ልጅ መሪየም ሳልዲቅ አልማሃዲ ተሰጥቷል፡፡