የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት መሪዎች በሶማሊያ ፕሬዝዳንት በዓለ ሲመት ላይ ለመታደም በመግባት ላይ ናቸው
እስካሁን የግብጽ እና የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትሮችን ጨምሮ በርካታ መሪዎች ሞቃዲሾ ደርሰዋል
ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ ከ15 ቀናት በፊት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል
የአፍሪካ እና የአረብ ሀገራት መሪዎች በሶማሊያ ፕሬዝዳንት በዓለ ሲመት ላይ ለመታደም በመግባት ላይ ናቸው፡፡
ሶማሊያን በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በፕሬዝዳንትነት እንዲመሩ የተመረጡት ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ በዓለ ሲመት ዛሬ ይካሄዳል፡፡
በሀገሪቱ መዲና ሞቃዲሾ በሚካሄደው በዚህ በዓለ ሲመት ላይ ለመሳተፍ የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ወደ ስፍራው አምርተዋል፡፡
እስካሁን የኢትዮጵያ እና ግብጽ ጠቅላይ ሚኒስትሮች አብይ አህመድ እና ሞስጠፋ ማድቡሊ አስቀድመው ሞቃዲሾ የደረሱ ሲሆን የተባበሩት አረብ ኢምሬት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሼክ ሻክቡት ቢን አል ናህያን ሞቃዲሾ ገብተዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የጅቡቲ፣ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያ እና የሌሎች ሀገራት መሪዎችም በአዲሱ ፕሬዝዳንት በዓለ ሲመት ላይ ለመገኘት በስፍራው ደርሰዋል፡፡
ለመሪዎቹ የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር መሀመድ ሀሰን ሮብል አቀባበል በማድረግ ላይ ሲሆኑ የተጨማሪ ሀገራት መሪዎች ወደ ሞቃዲሾ እንደሚመጡ ይጠበቃል፡፡
የአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ በዓለ ሲመት በሶማሊያ አየር ሀይል ዋና ማዘዣ በሆነው ሞቃዲሾ አውሮፕላን ጣቢያ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ ከሶስት ሳምንት በፊት የቀድሞውን ፕሬዝዳንት መሀመድ ፋርማጆን ተክተው መመረጣቸው ይታወሳል፡፡