ፕሬዝዳንት ሙን፣ ኪምን ከተመራጩ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ የኦል እና ከአሜሪካ ጋር ንግግር እንዲጀምሩ ጠይቀዋል
የሰሜን ኮሪያ መሪ ኮም ጆንግ ኡን እና የደቡብ ኮሪያ መሪ እና በቅርቡ ስልጣን የሚለቁት ሙን ጄይ ባለፈው ሳምንት ደብዳቤ መቀያየራቸውን ፕዮንግያንግ እና ሲኦል አረጋግጠዋል፡፡
ሀለቱ መሪዎች ደብዳቤ የተጻጻፉት፤ሁለቱ ሀገራት በፈረንጆቹ 2019 አሜሪካና እና ደቡብ ኮሪያ ያዘጋጁት ስብሰባ ያለስኬት ከተጠናቀቀ እና ሰሜን ኮሪያ ባለፈው ወር ያስወነጨፈችውን አህጉር አቋራጭ ሚሳየል ተከትሎ የተፈጠረው የድንበር ውዝግብ በቀጠለበት ወቅት ነው፡፡
ሲጂቲኤን የሰሜን ኮሪያን ሚዲያ ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ባለፈው ረብኡ ከደቡብ ኮሪያው ሙን የግል ደብዳቤ እንደተላከላቸው እና በቀጣዩ ቀንም ሙን በሁለቱ ኮሪያውን መካከል ያውን ግንኙነት ለማሻሻል በሞካራቸው በማመስገን ደብዳቤ ልከዋል፡፡
እንደዘገባው ከሆኑ ኪም ሁለቱ ኮሪያዎች ግንኙነት ይሻሻላል የሚል ተስፋ እንዳላቸው ለሙን ተናግረዋል፡፡ ኪም፣ ሙን እስመጨረሻው የስልጣን ዘመናቸው ለሀሪቱ መልካም ነገር ለመስራት መጣራቸውን አድንቀዋል፡፡
ሁለቱ መሪያዎች፤ ሁለቱም ወገኖች ጠንክረው የሚሰሩ ከሆነ የሁለቱ ኮሪያዎች ግንኙነት ሊዳብር እና ሊያድግ ይችላል ብለዋል፡፡
ሁለቱ መሪዎች የወዳጅነት ደብዳቤ መቀያየራቸውን ያረጋገጠው የሙን ቢሮም፤ ሙን ለሁለቱ ኮሪያዎች ግንኙነት ኪም ቁርጠኛ እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ሙን፣ ኪም ከአዲሱ የደቡብ ኮሪያ ተመራጭ ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ የኦል እና ከአሜሪካ ጋር በቶሎ ንግግር እንዲጀምሩ መጠየቃቸው ተዘግቧል፡፡