ሰሜን ኮሪያ በደቡብ ኮሪያ ሴኦል ያሉ ቦታዎችን ልታወድም እንደምትችል አስጠንቅቃለች
ሱህ ከሰሜን ኮሪያ የሚያቃጣውን ስጋት ለመቋቋም እንዲችል ለጦራቸው በቂ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል
ሰሜን ኮሪያ በየካቲት ወር ባሊስቲክ ሚሳኤል መተኮሷን ተከትሎ በኮሪያ ባህር ሰላጤ ያለው ውጥረት አይሏል
ሰሜን ኮሪያን የመምታት አቅም አለን በማለት አስተያየት የሰጡትን የደቡብ ኮሪያውን መከላከያ ሚኒስቴር ያወገዘችው፣ ሰሜን ኮሪያ ጥቃት የሚሰነዘርባት ከሆነ በሴኦል ያሉ ትላልቅ ቦታዎች እንደምታወድም አስጠንቅቃለች፡፡
የሰሜን ኮሪያው መሪ ወንድም የሆኑት ኪም ዮ ጆንግ የደቡብ ኮሪያው መከላከያ ሚኒስትር አስተያየት የሁለቱ ኮሪያዎችም ግንኙነትና እና በኮሪያ ባህረ ሰላጤ ያለው ውጥረት የበለጠ ያባብሰዋል ማታቸውን ሮይተርስ የሀገሪቱን ሚዲያ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡
ኪም ዮ ጆንግ ይህን ያሉት የደቡብ ኮሪያው ሚኒስትር ሱ ሁክ ባለፈው አርብ እለት የሀገራቸው ጦር በእጅጉ የተሻሻለ መሆኑን እና በሰሜን ኮሪያ ውስጥ ያለ የትኛውንም ቦታ በፍጥነትን በትክክል መምታት ይችላል ማለታቸውን ተክትሎ ነው፡፡
ሱህ ከሰሜን ኮሪያ የሚያቃጣውን ወታደራዊ ስጋት ለመቋቋም እንዲችል ለጦራቸው በቂ ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል፡፡
ሱህ ሰሜንን ጠላት ሲሉ ጠርተዋል፡፡
የኮሪያው የሰራተኛ ፓርቲ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ኪም፤ በዚህ አይነት አስተያየት ደቡብ ኮሪያ አደጋ ሊደርስባት እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ የፓርቲው ጸሃፊ የሆኑት ፓክ ጆንግ ቾን ሰሜን ኮሪያ ያላት ጦር ሁሉ በመጠቀም በደቡብ ኮሪያ ሴኦል ያሉ ቦታ ልታወድም ትችላለች፤ ይህ የመሆነው ግን የደቡብ ኮሪያ ጦር የሚተነኩስ ከሆነ ነው ብለዋል፡፡
ሰሜን ኮሪያ በየካቲት ወር ባሊስቲክ ሚሳኤል መተኮሷን ተከትሎ በኮሪያ ባህር ሰላጤ ያለው ውጥረት አይሏል፡፡