የአየር ንብረት ለውጥና ድህነት የዘመናችን የህልወና አደጋ ናቸው- የሀገራት መሪዎች
መሪዎቹ በጋራ በመሆን ለህዝብ እና ለዓለም ለማበርከት በፍጥነት መስራት እንዳለባቸውም ተናግረዋል
መሪዎቹ ባለፉት ስሶት አመታት 120 ሚሊዮን ህዝብ ወደከፋ ድህነት መግባቱን እና በዚህም የዘላቂ ልማት ግቦችን ማሳካት እንዳልተቻለ ገልጸዋል
የአረብ ኢምሬትሱን መሃመድ ቢንዛይድ አልነሃያንን፣ የፈረንሳዩን ኢማንኤል ማክሮንን እና የአሜሪካውን ጆ ባይደንን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት መሪዎች የአየር ንብረት ለውጥና እና ድህነት የህልውና ስጋት መሆናቸውን ገልጸዋል።
መሪዎቹ በጋራ በመሆን ለህዝብ እና ለዓለም ለማበርከት በፍጥነት መስራት እንዳለባቸውም ተናግረዋል።
በርካታ እና ተደራራቢ ችግሮች የሀገራትን ድህነትን እና ርሃብን የመቅረፍ አቅማቸውን ችግር ውስጥ እንዳስገባው የገለጹት መሪዎቹ የደሃ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ሀገራት የብድር ተጋላጭነት ኢኮኖሚያቸው እንዳይሻሻል ዋነኛ እንቅፋት ነው ብለዋል።
ሀገራቱ ባለፉት ስሶት አመታት 120 ሚሊዮን ህዝብ ወደከፋ ድህነት መግባቱን እና በዚህም የዘላቂ ልማት ግቦችን ማሳካት እንዳልተቻለ ገልጸዋል።
ግቦቹን ለማሳካት ኢፍትሃዊነትን እና ድህነትን መዋጋት እንደለባቸው መሪዎቹ ገልጸዋል።
መሪዎቺ እንዳሉት የእድገት ፍላጎቶችን እና ተጋላጭነትን ከግምት ያስገባ ስርአት ያስፈልጋል ብለዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ በደሃና በጣም ደሃ በሆኑ ሀገራት ላይ ትልቅ እና ተደጋጋሚ አደጋ እንደሚያስከትል የገለጹት መሪዎቹ ችግሩን ለመፍታት የሚስማማ ስርአት መኖር አለበት ብለዋል።
የፖሪሱ የአየርንብረት ስምምነት ይህ ትውልድ የዘላቂ የልማት ግቦችን እንዲያሳካ መልከም አጋጣሚ እንደሚሆንለት መሪዎቹ ገልጸዋል።
ሁሉንም ያማከለ የልማት ሽግግር ደህነትን ለማቃለል እና ዘላቂ ልማትን ለማምጣት ጠንካራ ኃይል እንደሚሆን ተናግረዋል መሪዎቹ።
መሪዎቹ እንዳሉት በከባድ ችግሮ ውስጥ ላሉ ሀገራት የሚሆን 100 ቢሊዮን ዶላር ከበጎ ፍቃደኞች የመሰብሰብ ፍላጎት አላቸው።