የያዝነው አስር ዓመት ለአየር ንብረት ለውጥ ወሳኝ ጊዜ እንደሆነ ተገለጸ
የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ውጤታማ እና በበጎ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ ጥረት ያስፈልጋል
በፈረንጆቹ 2030 ላይ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን ካርበን ለመቀነስ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ያለንበት ጊዜ ወሳኝ ነው ተብሏል
የያዝነው አስር ዓመት ለአየር ንብረት ለውጥ ወሳኝ ጊዜ እንደሆነ የተባሩት ምንግስታት ድርሀት አስታወቀ።
በተመድ የኮፕ28 አየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ መሪ የሆኑት ራዛን አል ሙባረክ እንዳሉት የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ውጤታማ እና በበጎ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ ጥረት ያስፈልጋል ብለዋል።
ራዛን አል ሙባረክ በጀርመን ቦን ከተማ እየተካሄደ ባለው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ያለንበት ወቅት የአየር ንብረት ለውጥ ጥያቄዎችን ከመመለስ አንጻር ዋነኛው ነው ብለዋል።
በፈረንጆቹ 2030 ላይ ወደ ከባቢ አየር የሚለቀቀውን ካርበን ለመቀነስ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት ያለንበት ጊዜ ዋነኛው መሆኑንም አክለዋል።
በተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ አንድ አካል የሆነው ይህ የቦን ከተማ ጉባኤ የፊታችን ህዳር በአረብ ኢምሬት ለሚካኬደው ዓለም አቀፍ ጉባኤ የውሳኔ ሀሳቦች የሚቀርቡበትም ነው ተብሏል።
በቦኑ ጉባኤ በተለይም በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የደረሱ ጉዳቶች እና ካሳ ክፍያን በሚመለከት የመጨረሻ የውሳኔ ሀሳብ መስጠት፣ በቀጣይ የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳትን መቀነስ የሚያስችሉ አዳዲስ እርምጃዎች የሚቀርቡበት እንደሚሆንም ተገልጿል።