በግብርና ከፍተኛ ገቢ የሚያገኙ የአለም ሀገራት
በአመት ከአንድ ቢሊየን ቶን በላይ የግብርና ምርት የምታመርተው ቻይና 1.5 ትሪሊዮን ዶላር ገቢ በማግኝት ከአለም ቀዳሚዋ ናት
የግብርና ዘርፍ አሁንም የጠንካራ ኢኮኖሚ መገለጫ ሆኖ ቀጥሏል
በቀደመው የሰው ልጅ ታሪክ አደን ላይ ከተመሰረተ ኑሮ ወደ ግብርና ከተሸጋገረበት ግዜ አንስቶ ግብርና የጠንካራ ኢኮኖሚ መገለጫ ሆኖ ቀጥሏል፡፡
ሀገራት እንደየሚገኙበት መልክአምድር እና የአየር ጸባይ ሁኔታ እራሳቸውን ለመመገብ አልፎም ለውጭ ሀገራት ገበያ በሚያቀርቡት የግብርና ምርት ኢኮኖሚቸው ተወዳዳሪ እንዲሆን ማስቻል ችለዋል፡፡
በአለም አቀፍ ደረጃ አትክልት እና ፍራፍሬን ጨምሮ ፣ ጥራጥሬ እንዲሁም የእህል ዘሮችን በማምረት እራሳቸውን መመገብ የቻሉ ሀገራት በውጭ ሀገራት ላይ ያለቸውን ጥገኝነት በመቀነስ ብርቱ ምጣኔ ሀብትን ለመፍጠር ግብርናን በሰፊው ተጠቅመውበታል፡፡
በአመት ከአንድቢሊዮን ቶን በላይ ምርት የምታመርተው ቻይና ቀዳሚዋ የግብርና ምርት አምራች ሀገር ናት፤ በተጨማሪም ከዘርፉ በአጠቃላይ በአመት 1.5 ትሪሊዮን ዶላር በመሰብሰብ ከግብርና ከፍተኛ ገቢ በማግኝት ከአለም ቀዳሚዋ ናት፡፡
ሩዝ ፣ ስንዴ ፣ በቆሎ እና ድንች ሀገሪቱ በስፋት ከምታመርታቸው የግብርና ምርቶች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡
412 ቢሊየን ዶላር በአመት የምታገኝው ህንድ በበኩሏ በግብርና ገቢ በሁለተኛ ደረጃ ስትቀመጥ የቅባት እህሎች ፣ ማሽላ ፣ ሩዝ ፣ ስንዴ እና አትክልትን በከፍተኛ ሁኔታ ታመርታለች፡፡