ልዩልዩ
የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን የሚያስተምረው መተግበሪያ
አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሶማሊኛ እና ትግርኛ ቋንቋዎችን በድምጽ እና በጽሁፍ የሚያስተምረው መተገበሪያ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የበለጸገ ነው
መተግበሪያው ድምጽን ወደ ጽሁፍ መቀየርም ያስችላል ተብሏል
የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን ለመማር የሚረዳ መተግበሪያ ተዋወቀ።
መተግበሪያው በሰው ሰራሽ አስተውሎት ወይም አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ የበለጸገ ነው ተብሏል።
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ያበለጸገው መተግበሪያ አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሶማሊኛ እና ትግርኛ ቋንቋዎችን በድምጽ እና በጽሁፍ ለመማር ያስችላል፡፡
መተግበሪያው ድምጽን ወደ ጽሁፍ መቀየርም የሚያስችል ተጨማሪ ክፍል አለው።
ድምጽን በመቅዳት ወይም ከመዛግብት (አርካይቭ) የድምጽ ፋይሎችን ወደመተግበሪያው በማስገባት የጽሁፍ ቅጂውን ማግኘት ይቻላል ብሏል ኢንስቲትዩቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ።
መተግበሪያውን ከጉግል ፕሌይ ስቶር ማግኘት እንደሚቻልም ነው ተቋሙ ያስታወቀው።
ይህን ማስፈንጠሪያ በመጫን መተግበሪያውን ማግኘት ይቻላል።
መተግበሪያውን ከጉግል ፕሌይ ስቶር አውርዶ ለመጠቀም ቪ.ፒ.ኤን (VPN) ማጥፋት እንደሚገባ ተገልጿል።